ኅዳር 2, 2023
ሜክሲኮ
ኦቲስ የተባለ አውሎ ነፋስ የሜክሲኮን ደቡብ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ መታ
ጥቅምት 25, 2023 ኦቲስ የተባለ በአምስተኛ እርከን ሥር የተመደበ አውሎ ነፋስ የቱሪስት ከተማ በሆነችው በአካፑልኮ አቅራቢያ የሚገኘውን የሜክሲኮን ደቡብ ምዕራባዊ የባሕር ዳርቻ መታ። ከዚህ ቀደም የፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢን ከመቱት አውሎ ነፋሶች መካከል በአጭር ጊዜ ውስጥ በዚህ መጠን ኃይለኛ የሆነ አውሎ ነፋስ ተመዝግቦ አያውቅም። በሰዓት ከ265 ኪሎ ሜትር በላይ ፍጥነት የነበረው ይህ ዝናብ የቀላቀለ አውዳሚ አውሎ ነፋስ ከባድ ጎርፍም አስከትሏል። አውሎ ነፋሱ በመንገዶች፣ በሕንፃዎችና በመሠረተ ልማት ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት እንዳስከተለ ሪፖርት ተደርጓል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸዋል። ቢያንስ 45 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በአካባቢው የሚኖሩ ወንድሞች አውሎ ነፋሱ በተከሰተበት ጊዜ የሚከተሉትን መረጃዎች ልከውልናል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የሞተ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም
አደጋው በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩ ከ10,000 የሚበልጡ ወንድሞችና እህቶች አሉ
በአካፑልኮ ያለ 1 የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች አደጋው በደረሰበት አካባቢ ለሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው
በማዕከላዊ አሜሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ የሚያገለግሉ 4 ተወካዮች አካባቢውን በመጎብኘት ማበረታቻና ድጋፍ ሰጥተዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴውን የሚከታተል የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተመድቧል
ይሖዋ፣ ኦቲስ በተባለው አውሎ ነፋስ ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞችና እህቶች ሰላምና መጽናኛ እንዲሰጣቸው እንጸልያለን።—ፊልጵስዩስ 4:6, 7