በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 10, 2022
ሜክሲኮ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በናዋትል ቋንቋ (የሰሜን ፕዌብላ) ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በናዋትል ቋንቋ (የሰሜን ፕዌብላ) ወጣ

ሰኔ 5, 2022 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በናዋትል ቋንቋ (የሰሜን ፕዌብላ) ወጣ፤ የዚህ ትርጉም የታተመም ሆነ ኤሌክትሮኒክ ቅጂ መውጣቱን ያበሰረው የማዕከላዊ አሜሪካ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ኤድዋር በን ነው። አስቀድሞ የተቀዳውን ፕሮግራም ከ1,500 የሚበልጡ ተሰብሳቢዎች በቀጥታ ተከታትለውታል።

ናዋትል (የሰሜን ፕዌብላ) በዋነኝነት የሚነገረው ፕዌብላ እና ቬራክሩዝ በተባሉት የሜክሲኮ ግዛቶች ነው። በናዋትል (የሰሜን ፕዌብላ) የመጀመሪያዎቹ ጉባኤዎች የተቋቋሙት በ2002 ነው። በዚህ ቋንቋ የሚያገለግሉት አስፋፊዎች ይጠቀሙበት የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ የይሖዋን ስም “ጌታ” እና “አምላክ” በሚሉት የማዕረግ ስሞች ተክቶታል።

ወንድም በን በንግግሩ ላይ እንዲህ ብሏል፦ “የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ትርጉምን ከአሁን ጀምሮ እንድታነቡት እናበረታታችኋለን። ይህ ትርጉም የአምላክን መልእክት በቋንቋችሁ በትክክል እንደሚያስተላልፍ ሙሉ በሙሉ መተማመን ትችላላችሁ።”

ይህ ትርጉም፣ ናዋትል (የሰሜን ፕዌብላ) ተናጋሪ የሆኑ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እንደሚያጠናክራቸው ብሎም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ሲሰብኩ በእጅጉ እንደሚያግዛቸው እንተማመናለን።—ማርቆስ 13:10