በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኅዳር 3, 2021
ሜክሲኮ

ፓሜላ የተባለው አውሎ ነፋስ በሜክሲኮ የፓስፊክ ዳርቻ ጎርፍ አስከተለ

ፓሜላ የተባለው አውሎ ነፋስ በሜክሲኮ የፓስፊክ ዳርቻ ጎርፍ አስከተለ

ጥቅምት 13, 2021 የሜክሲኮ ዳርቻ በሃሪኬን ፓሜላ ተመታ። አውሎ ነፋሱ በዋነኝነት በዱራንጎ፣ በናያሪት እና በሲናሎዋ አካባቢዎች ከባድ ዝናብና የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችን መካከል አካላዊ ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 112 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 75 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • ወንድሞቻችን ሪፖርት እንዳደረጉት ድርጅቱ ከተፈጥሮ አደጋዎች ጋር በተያያዘ ማሳሰቢያ ሰጥቶ ስለነበር ለአደጋው የተሻለ ዝግጁነት ነበራቸው

  • ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት ወንድሞች፣ በዘመዶቻቸው ወይም በእምነት ባልንጀሮቻቸው ቤት ተጠግተዋል

  • 20 አስፋፊዎች የምግብ እርዳታ ተሰጥቷቸዋል

  • በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ክርስቲያኖች እረኝነት እያደረጉ ነው

  • ሁሉም የእርዳታ እንቅስቃሴ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ጉዳት የደረሰባቸውን ወንድሞች ለመርዳት የተወሰደው አፋጣኝ እርምጃ ይሖዋ ለእነሱ ያለውን ፍቅርና አሳቢነት በግልጽ ያሳያል። አምላካችን በእርግጥም “አስተማማኝ መጠጊያ” ነው።—መዝሙር 59:16