በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሳይ አሸር የመታሰቢያውን በዓል ንግግር ሲሰጥ

ሚያዝያ 21, 2021
ምያንማር

የ2021 የመታሰቢያው በዓል አከባበር—ምያንማር

ሕዝባዊ ዓመፅ በመቀስቀሱ ምክንያት የመታሰቢያው በዓል ንግግር በስልክ ተላለፈ

የ2021 የመታሰቢያው በዓል አከባበር—ምያንማር

ከየካቲት 2021 አንስቶ ምያንማር በሕዝባዊ ዓመፅ ስትታመስ ቆይታለች። ከክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በፊት በነበሩት ሳምንታት ታጣቂዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጦርነት ከፍተው ነበር። በዚህም የተነሳ በምያንማር ካሉት 5,102 አስፋፊዎች መካከል አብዛኞቹ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦባቸው ነበር። በመሆኑም ወንድሞች የመታሰቢያውን በዓል ንግግር በስልክ አማካኝነት ተከታትለዋል።

በአንድ ከተማ የመታሰቢያው በዓል በሚከበርበት ዕለት ከባድ ተኩስ ተከፈተ። ወታደሮች በየቤቱ እየሄዱ ተቃዋሚዎችን ማደን ጀመሩ። ወንድሞች በኢሳይያስ 30:15 ላይ የሚገኘውን ‘ሳትረበሹ፣ ተማምናችሁ ኑሩ’ የሚለውን የዓመት ጥቅስ ማስታወሳቸው አጽናንቷቸዋል። ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ዝቅ በማድረግና የመብራታቸውን ብርሃን በማደብዘዝ ከቤታቸው ሳይወጡ የመታሰቢያውን በዓል በሰላም ማክበር ችለዋል። ሕዝባዊ ዓመፅ ቢኖርም ጉባኤው እስካሁን ከነበረው ሁሉ ከፍተኛውን የመታሰቢያ በዓል ተሰብሳቢዎች ቁጥር አስመዝግቧል። ብዙዎች ንግግሩን በስልክ አዳምጠዋል።

በአገሪቱ በአጠቃላይ 11,877 ሰዎች የመታሰቢያውን በዓል ያከበሩ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2019 ከተመዘገበው ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር በ14 በመቶ ይበልጣል።

የኢንተርኔት አገልግሎት ያላቸው ሁለት እህቶች የመታሰቢያውን በዓል ንግግር በኤሌክትሮኒክ መሣሪያቸው ሲከታተሉ። ድምፁን ከፍ አድርገው በመክፈት ንግግሩን በስልክ ለሚያዳምጡ ሰዎች እያስተላለፉ ነው

በሰማይ ያለው አባታችን ይሖዋ ወንድሞቻችን ሕዝባዊ ዓመፅ ቢኖርም መንፈሳዊ እንቅስቃሴያቸውን ለመቀጠል ያደረጉትን ቁርጥ ውሳኔ ሲመለከት በጣም እንደሚደሰት እርግጠኞች ነን።—ምሳሌ 27:11