በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ቸላነ የተባለው አውሎ ነፋስ የሞዛምቢክን የባሕር ዳርቻ ሲመታ

ጥር 13, 2021
ሞዛምቢክ

ቸላነ የተባለው አውሎ ነፋስ ሞዛምቢክን መታ

ቸላነ የተባለው አውሎ ነፋስ ሞዛምቢክን መታ

ቦታ

በማዕከላዊ ሞዛምቢክ የሚገኙት ሶፋላ እና ማኒካ የተባሉት ግዛቶች፤ ከተጎዱት አካባቢዎች መካከል መጋቢት 2019 ኢዳይ በተባለው አውሎ ነፋስ የተጎዱት አካባቢዎችም ይገኙበታል

የደረሰው አደጋ

  • ቸላነ የተባለው አውሎ ነፋስ ታኅሣሥ 30, 2020 የሞዛምቢክን የባሕር ዳርቻ መታ። አደጋው ያስከተለው ጎርፍና ከዚያ በኋላ የተከሰተው የመሬት መንሸራተት መጠነ ሰፊ ጉዳት አስከትሏል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ሦስት አስፋፊዎች መጠነኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 34 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 12 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 16 ቤቶች ፈርሰዋል

  • 7 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 4 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ፈርሷል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የእርዳታ ሥራውን የሚያስተባብር የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል፤ የእርዳታ ሥራው በአደጋው ምክንያት ቤታቸው የፈረሰባቸው አስፋፊዎች ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲያገኙ ማድረግን ይጨምራል። የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ይሖዋ በዚህ አውሎ ነፋስ የተጎዱ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን መርዳቱን እንዲቀጥል እንጸልያለን።—መዝሙር 121:2