በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 6, 2022
ሞዛምቢክ

አዲስ ዓለም ትርጉም በሴና ቋንቋ ወጣ

አዲስ ዓለም ትርጉም በሴና ቋንቋ ወጣ

የሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ዴቪድ አሞሪም ጥቅምት 2, 2022 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በሴና ቋንቋ መውጣቱን አበሰረ። a በርካታ አስፋፊዎች፣ ወንድም ዴቪድ መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን ያበሰረበትን አስቀድሞ የተቀዳ ንግግር በየስብሰባ አዳራሾቻቸው ሆነው ተከታትለውታል። ፕሮግራሙ በብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያና በ14 የሬዲዮ ጣቢያዎች ላይም ተላልፏል።

ሴና፣ ሞዛምቢክ ውስጥ ባሉ አራት ግዛቶች ማለትም በማኒካ፣ በሶፋላ፣ በቴቴ እና በዛምቤዚያ የሚነገር ቋንቋ ነው። በተጨማሪም በማላዊ ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ይነገራል።

ቤይራ፣ ሞዛምቢክ ውስጥ የሚገኘው የሴና የርቀት የትርጉም ቢሮ

የይሖዋ ምሥክሮች በቀደምት የአገሬው ቋንቋ ሙሉውን አዲስ ዓለም ትርጉም ሲያወጡ ይህ የመጀመሪያቸው ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ከመውጣቱ በፊትም የመጽሐፍ ቅዱስን የተወሰኑ ክፍሎች የያዙ ሌሎች ትርጉሞች ነበሩ፤ ሆኖም በጣም ውድና የተረሱ ቃላትን የሚጠቀሙ ናቸው።

የሴና ቋንቋ ተናጋሪ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ይህን ልዩ በረከት ከይሖዋ በማግኘታቸው የደስታቸው ተካፋዮች ነን።—ምሳሌ 10:22

a መጽሐፍ ቅዱሱ በወረቀት ታትሞም ሆነ በኤሌክትሮኒክ ፎርማት ቀርቧል