በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ፦ በቺፓንጋራ ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ፤ ከታች በስተ ግራ፦ በሶፋላ ግዛት የደረሰው መጥለቅለቅ፤ ከታች በስተ ቀኝ፦ በሙሹንጌ ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ

የካቲት 9, 2021
ሞዛምቢክ

ኢሎይስ የተባለው አውሎ ነፋስ በሞዛምቢክ ከባድ ውድመት አስከተለ

ኢሎይስ የተባለው አውሎ ነፋስ በሞዛምቢክ ከባድ ውድመት አስከተለ

ቦታ

የጋዛ፣ ኢንያምባኔ፣ ማኒካ፣ ሶፋላ እና ዛምቤዚያ ግዛቶች

የደረሰው አደጋ

  • ጥር 23, 2021 ኃይለኛ ነፋስና ከባድ ዝናብ በሞዛምቢክ በሚገኙ አምስት ግዛቶች ላይ መጠነ ሰፊ ውድመት አስከትሏል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 3 አስፋፊዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 13 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 9 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 9 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 3 የስብሰባ አዳራሾች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል

  • 53 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 41 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 10 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • አደጋው ከመድረሱ በፊት የሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ቢሮ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ አስፋፊዎች በሙሉ መኖሪያቸውን ለቀው ከአደጋው ቀጠና ውጭ ወደሆነ አካባቢ እንዲሄዱ አሳስቦ ነበር

  • ቅርንጫፍ ቢሮው ለተፈናቃዮች ጊዜያዊ መጠለያ ማመቻቸትን ጨምሮ የእርዳታ ሥራውን ለማስተባበር አራት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል

  • አደጋው በተከሰተበት አካባቢ ያሉት የወረዳ የበላይ ተመልካቾች አስፋፊዎችን እየረዱና እያበረታቱ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

የአምላክ መንግሥት የተፈጥሮ አደጋዎችንና የሚያስከትሉትን መከራ የሚያስወግድበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።—ማቴዎስ 6:10