በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሐምሌ 13, 2023
ሞዛምቢክ

የማቴዎስ ወንጌል በሞዛምቢክኛ ምልክት ቋንቋ ወጣ

የማቴዎስ ወንጌል በሞዛምቢክኛ ምልክት ቋንቋ ወጣ

ሐምሌ 9, 2023 በማፑቶ፣ ሞዛምቢክ በተደረገ ልዩ ስብሰባ ላይ የማቴዎስ ወንጌል በሞዛምቢክኛ ምልክት ቋንቋ ወጣ። የመጽሐፉን መውጣት ያበሰረው የሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ካስትሮ ሳልቫዶ ሲሆን ፕሮግራሙን 857 ታዳሚዎች በአካልና በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተከታትለውታል። መጽሐፉን JW Library Sign Language ከተባለው አፕሊኬሽን እና ከ​jw.org ላይ ማውረድ ይቻላል።

በሞዛምቢክ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን መስማት የተሳናቸው የይሖዋ ምሥክሮች ፍላጎት ለማሟላት ሲባል በ2017 በማፑቶ በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ የሞዛምቢክኛ ምልክት ቋንቋ ትርጉም ቡድን ተቋቋመ። በአሁኑ ወቅት በሞዛምቢክ ባሉት 5 የምልክት ቋንቋ ጉባኤዎች፣ 12 ቡድኖችና 10 ቅድመ ቡድኖች ውስጥ 344 አስፋፊዎች ያገለግላሉ።

የማቴዎስ ወንጌል፣ በሞዛምቢክኛ ምልክት ቋንቋ የወጣው የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ነው። ከተርጓሚዎቹ አንዱ እንዲህ ብሏል፦ “በሞዛምቢክኛ ምልክት ቋንቋ የሚጠቀሙ ሰዎች የናሙናውን ጸሎት በራሳቸው ቋንቋ አንብበውት አያውቁም። ማቴዎስ 6:9-13⁠ን በመጠቀም ጸሎት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቼ ለማስረዳት ጓጉቻለሁ።”

ይህ መጽሐፍ፣ በሞዛምቢክ ያሉ ቅን ልብ ያላቸው በርካታ ሰዎች ስለ “አምላክ ቅዱስ ቃል” ለመማር እንደሚያስችላቸው ማወቃችን አስደስቶናል።—ሮም 3:2