በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 24, 2022
ሞዛምቢክ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በሎምዌ ቋንቋ ወጣ

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት በሎምዌ ቋንቋ ወጣ

ሰኔ 19, 2022 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም በሎምዌ ቋንቋ መውጣቱን የሞዛምቢክ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ፓትሪክ ሄከር አብስሯል። አስቀድሞ በተቀረጸ ፕሮግራም ላይ መጽሐፍ ቅዱሱ በኤሌክትሮኒክ ፎርማት መውጣቱ ተገልጾ ነበር። በሎምዌ ቋንቋ በሚመሩት ጉባኤዎች ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ አስፋፊዎች ፕሮግራሙን የተከታተሉት በስብሰባ አዳራሾቻቸው ውስጥ ሲሆን በዚያ የተገኘው እያንዳንዱ ሰው የመጽሐፍ ቅዱሱን የታተመ ቅጂም ማግኘት ችሏል።

ከ1930 ጀምሮ በሎምዌ ቋንቋ የተተረጎሙ መጽሐፍ ቅዱሶች ይገኙ ነበር፤ ሆኖም ዋጋቸው ውድ ከመሆኑም ሌላ የሚጠቀሙት ጥንታዊ ቃላትን ነው። ሌላው ችግር ደግሞ መልእክቱን በትክክል የማያስተላልፉ መሆኑ ነው። ለምሳሌ ሉቃስ 23:43 “እውነት እልሃለሁ ዛሬ፣ ከእኔ ጋር በሰማይ ትሆናለህ” ተብሎ ተተርጉሟል። አዲስ ዓለም ትርጉም ግን “እውነት እልሃለሁ ዛሬ፣ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” በማለት መልእክቱን በትክክል አስቀምጦታል።

በሙዤባ ጉባኤ የሚገኙ አስፋፊዎች መጽሐፍ ቅዱሶቻቸውን እያሳዩ

ከተርጓሚዎቹ አንዱ ስለ አዲሱ ትርጉም ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “በሎምዌ ቋንቋ የተዘጋጀው የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም ግልጽና ለማንበብ ቀላል ነው። ወንድሞች ቅዱሳን መጻሕፍትን መረዳት ቀላል እንደሚሆንላቸውና የተማሩትንም ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚነሳሱ ጥያቄ የለውም።”

ይህ አዲስ ትርጉም ወንድሞችና እህቶች የራሳቸውን መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላትና በአገልግሎት ላይ ሰዎችን ለመርዳት እንደሚያግዛቸው እንተማመናለን።—ማቴዎስ 5:3