ጥር 27, 2022
ሩሲያ
ሁለት ወንድሞች የይሖዋን እጅ በማየታቸው በድፍረት ጸንተዋል
በታምቦቭ ክልል የሚገኘው የኪርሳኖቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የወንድም አንቶን ኩዤልኮቭን እና የወንድም ኒኮላይ ፕሮኮሮቭን ጉዳይ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔውን ያሳውቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
የክሱ ሂደት
ታኅሣሥ 21, 2020
አንቶን እና ኒኮላይ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ አደራጅተዋል በሚል የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው
ታኅሣሥ 24, 2020
መርማሪዎች የአንቶንን ቤት ጨምሮ 19 ቦታዎችን ፈተሹ። አንቶን ከቤቱ 350 ኪሎ ሜትር ርቆ ወደሚገኝ ቦታ ለምርመራ ተወሰደ። ኒኮላይም ምርመራ ተደረገበት፤ ከዚያም አካባቢውን ለቆ እንዳይሄድ ታዘዘ
ታኅሣሥ 25, 2020
አንቶን ወደ ቤቱ እንዲመለስ አልተፈቀደለትም፤ ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ
ነሐሴ 30, 2021
አንቶን ወደ ሌላ ማረፊያ ቤት ተዛወረ
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ስደት ለሚደርስባቸው ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ድፍረት መስጠቱንና እነሱን መደገፉን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ምሳሌ 1:33
a ወንድም ኩዤልኮቭ በአሁኑ ወቅት ማረፊያ ቤት ይገኛል። በመሆኑም የእሱን ሐሳብ መጠየቅ አልቻልንም።