በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሩሲያ የሚኖሩት እህት ካለሪያ ማሚኪና (78 ዓመት) በእምነታቸው ምክንያት ክስ ተመሥርቶባቸዋል

ሰኔ 26, 2019
ሩሲያ

ሩሲያ ከ70 ዓመት በላይ በሆናቸው አረጋውያን የይሖዋ ምሥክሮች ላይ ጥቃት እየሰነዘረች ነው

ሩሲያ ከ70 ዓመት በላይ በሆናቸው አረጋውያን የይሖዋ ምሥክሮች ላይ ጥቃት እየሰነዘረች ነው

በፐርም ከተማ የሚኖሩት ወንድም ቦሪስ ቡሪሎቭ (78 ዓመት) “ጽንፈኛ ናቸው” የሚል ክስ ተመሥርቶባቸዋል

የሩሲያ ክልሎች የሆኑት የአርሃንጌልስክ እና የቮልገግራት ባለሥልጣናት በግንቦት 2019 በሁለት አረጋውያን እህቶች ላይ ክስ መሠረቱ። ፍቶግራፋቸው ከላይ የሚታየው እህት ካለሪያ ማሚኪና (78 ዓመት) እና እህት ቫለንቲና ማኽመድጋይቫ (71 ዓመት) የይሖዋ ምሥክር በመሆናቸው ብቻ “የጽንፈኝነት” ድርጊት በመፈጸም ወንጀል ተከሰው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው።

በሚያዝያ 2018 የቭላዲቨስቶክ ከተማ ባለሥልጣናት 84 ዓመት በሆናቸው በእህት የሌና ዛይሹክ እና በሌሎች አራት የይሖዋ ምሥክሮች ላይ ክስ መሥርተው ነበር። በአሁኑ ወቅት ሩሲያ ውስጥ በሰላማዊ ሁኔታ ለይሖዋ አምልኮ በማቅረባቸው ምክንያት ክስ የተመሠረተባቸው ከ70 ዓመት በላይ የሆናቸው የይሖዋ ምሥክሮች ቁጥር አሥር ደርሷል።

ከእነዚህ አረጋውያን ክርስቲያኖች መካከል የታሰረ ባይኖርም የደረሰባቸው ነገር ለከፍተኛ ውጥረት እንደሚዳርጋቸው ጥያቄ የለውም። እነዚህ አረጋውያን ፍርድ ቤት ቀርበው ከተፈረደባቸው ደግሞ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ሊጣልባቸው ይቻላል ወይም ወህኒ ሊወርዱ ይችላሉ።

እስከ ሰኔ 17, 2019 ድረስ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ክስ የተመሠረተባቸው ወንድሞቻችን ቁጥር 215 ደርሷል። ይህ ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው። በሩሲያ ለሚገኙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አዘውትረን ልንጸልይላቸው ይገባል፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ስማቸውን ጠቅሰን ልንጸልይላቸው እንችላለን። ኃያል አምላክ የሆነው ይሖዋ እነዚህ ወንድሞቻችን ‘በትዕግሥትና በደስታ ሁሉንም ነገር በጽናት እንዲቋቋሙ የሚያስፈልጋቸውን ብርታት ሁሉ እንደሚሰጣቸው’ እንተማመናለን።—ቆላስይስ 1:11