በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የካቲት 11, 2020
ሩሲያ

ሩሲያ ውስጥ በወንድም ሚሃይል ፖፖቭ እና በባለቤቱ በእህት የሌና ፖፖቭ ላይ የተመሠረተው ክስ የካቲት 13, 2020 ፍርድ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል

ሩሲያ ውስጥ በወንድም ሚሃይል ፖፖቭ እና በባለቤቱ በእህት የሌና ፖፖቭ ላይ የተመሠረተው ክስ የካቲት 13, 2020 ፍርድ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል

የቪልዩቺንስክ ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም ሚሃይል ፖፖቭ እና በባለቤቱ በእህት የሌና ፖፖቫ ላይ የተመሠረተውን ክስ አይቶ ሐሙስ፣ የካቲት 13, 2020 ፍርድ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። ባልና ሚስቱ ሐምሌ 30, 2018 ላይ በካምቻትካ ከተማ ታስረው የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ተለቅቀዋል። ባልና ሚስቱ የተወነጀሉት ‘በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ” ሲካፈሉ ተገኝተዋል በሚል ክስ ነው።

ሚሃይል እና የሌና ይህን ፍርድ የሚጠባበቁት በይሖዋ በመታመን ነው። ይሖዋ ‘መጠጊያቸውና ብርታታቸው’ ሆኖ እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 46:1