በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን በፍርድ ቤቱ የእስረኞች ማቆያ ክፍል ውስጥ ሆኖ

ሐምሌ 9, 2020
ሩሲያ

ሩሲያ ውስጥ በወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ላይ የሰባት ዓመት እስር ሊፈረድበት ይችላል

ሩሲያ ውስጥ በወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ላይ የሰባት ዓመት እስር ሊፈረድበት ይችላል

በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የፉርማኖቭስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ሐምሌ 14, 2020 በወንድም ዬቭጌኒ ስፒሪን ላይ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ በወንድም ስፒሪን ላይ የሰባት ዓመት እስር እንዲበየንበት ጠይቋል።

የ34 ዓመቱ ወንድም ስፒሪን “የጽንፈኛ” ድርጅትን ሥራዎች በማስተባበር ወንጀል ተከሷል። ክሱን የመሠረተው የፌዴራል ደህንነት ቢሮ ሲሆን ክሱ የተመሠረተው ጥር 21, 2019 ነው። ከስድስት ቀናት በኋላ የፌዴራል ደህንነት አባላት በወንድም ስፒሪንና በባለቤቱ በናታሊያ ቤት ላይ ፍተሻ አካሂደዋል። በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የኦክትያብርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ስፒሪን የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ ብቻ፣ ቢያንስ ለሁለት ወር ያህል ችሎት ፊት ሳይቀርብ እንዲታሰር አዟል። በኋላም የእስር ጊዜው እንዲራዘም ተደርጓል።

እስር ቤት ውስጥ ለ160 ቀናት ያህል ከቆየ በኋላ ሐምሌ 5, 2019 ከእስር ቤት ወጥቶ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተወሰነበት። ታኅሣሥ 18, 2019 በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የኦክትያብርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ መርማሪዎቹ ተቃውሞ ቢያቀርቡም ወንድም ስፒሪን ከቁም እስር እንዲለቀቅ ትእዛዝ የሰጠ ሲሆን ተጨማሪ ገደብም አልጣለበትም።

በሰማይ ያለው አፍቃሪ አባታችን ይሖዋ በሩሲያ ውስጥ በእምነታቸው ምክንያት ስደት እየደረሰባቸው ካሉ ወንድሞቻችን ጋር እንደሚሆን በመተማመን ወደ እሱ መጸለያችንን እንቀጥላለን።—1 ጴጥሮስ 4:14