በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ሮማን ግሪዳሶቭ እና ባለቤቱ ኤልቪራ እንዲሁም ወንድም ጀናዲ ጀርመን እና ባለቤቱ ናዴዥዳ፤ ወንድሞች ልክ ከእስር እንደተፈቱ። ወንድሞች ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ቆይተዋል

ሐምሌ 30, 2021
ሩሲያ

ሩሲያ ውስጥ ታስረው የነበሩት ወንድም ጀናዲ ጀርመን እና ወንድም ሮማን ግሪዳሶቭ ተለቀቁ

ሩሲያ ውስጥ ታስረው የነበሩት ወንድም ጀናዲ ጀርመን እና ወንድም ሮማን ግሪዳሶቭ ተለቀቁ

ወንድም ጀናዲ ጀርመን እና ወንድም ሮማን ግሪዳሶቭ የተፈረደባቸውን እስር ጨርሰው ሐምሌ 29, 2021 ከእስር ተለቅቀዋል። እነዚህ ወንድሞች በኦረንበርግ እስር ቤት ሲደርሱ ከተደበደቡት አምስት የሳራቶቭ ወንድሞች መካከል ናቸው። ወንድም ፊሊክስ ማክሃማዲየቭ ጥር 2021፣ ወንድም አሌክሲ ቡደንቹክ ደግሞ ሐምሌ 2021 ከእስር ተለቅቀዋል። ወንድም አሌክሲ ሚረትስኪ ግን አሁንም ኦረንበርግ ውስጥ እስር ላይ ሲሆን ነሐሴ 2021 መጀመሪያ አካባቢ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።