በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ ባለቤቱ ስኔዣና እና እህት ቬራ ዞሎቶቫ

መስከረም 21, 2020
ሩሲያ

ሩሲያ ውስጥ ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ ባለቤቱ እና አንዲት የ73 ዓመት አረጋዊት እህት ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ሊፈረድባቸው ይችላል

ሩሲያ ውስጥ ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ ባለቤቱ እና አንዲት የ73 ዓመት አረጋዊት እህት ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ሊፈረድባቸው ይችላል

የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን

በካምቻትካ ክልል የሚገኘው የየሊዞቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ በባለቤቱ በስኔዣና እና በእህት ቬራ ዞሎቶቫ ላይ የቀረበውን ክስ ተመልክቶ መስከረም 25, 2020 a ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ ይዟል። አቃቤ ሕጉ ወንድም ኮንስታንቲንና ባለቤቱ 600,000 ሩብል (7,850 የአሜሪካ ዶላር) እህት ቬራ ደግሞ 400,000 ሩብል (5,235 የአሜሪካ ዶላር) እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

አጭር መግለጫ

ኮንስታንቲን ባዠኖቭ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1977 (ፔትሮፓቭሎቭስክ ካምቻትስኪ፣ ካምቻትካ ክልል)

  • ግለ ታሪክ፦ ከአራት ልጆች መካከል የመጀመሪያው ነው። ሜካኒክ ነበር፤ እንዲሁም ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ያስተምር ነበር። ዓሣ ማጥመድ ያስደስተዋል

  • በ2001 ስኔዣናን አገባ፤ እሷም መምህርት ነበረች። ኤሊዛቤት የምትባል ልጅ አለቻቸው። መላው ቤተሰብ ይሖዋን ያገለግላል

ስኔዣና ባዠኖቫ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1977 (ሺኮታን ደሴት፣ ሳካሊን ኦብላስት)

  • ግለ ታሪክ፦ በነጠላ ወላጅ ያደገች ነች። ልጆች ትወዳለች፤ እንዲሁም ትናንሽ ልጆችን ማስተማር ያስደስታታል። በተመሠረተባት ክስ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ልጆችን ማስተማር አይፈቀድላትም

  • ስለ አምላክና ስለ ጸሎት ያስተማረቻት አያቷ ነች። ይህም መንፈሳዊ ፍላጎት እንዲኖራትና ለመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር እንድታዳብር ረድቷታል

ቬራ ዞሎቶቫ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1946 (የሊዞቮ፣ ካምቻትካ ክልል)

  • ግለ ታሪክ፦ ያደገችው በትልቅ ቤተሰብ ውስጥ ነው። በ1966 ከዩሪ ዞሎቶቭ ጋር ትዳር መሠረተች። ሁለት ልጆች አሏቸው። ጡረታ የወጣች የሒሳብ ባለሙያ ነች። ተራራ መውጣትና የበረዶ ላይ ስፖርቶች ያስደስቷታል።

  • ለበርካታ ዓመታት ስለ አምላክ ለማወቅ ትሞክር ነበር። ብዙ ሃይማኖቶችን መርምራለች። በመጨረሻም አምላክ ፍትሐዊና ሰዎችን የሚወድ መሆኑን ስታውቅ በጣም ተደሰተች። ባለቤቷ የይሖዋ ምሥክር አልነበረም። ያም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ በእሷ ሕይወት ላይ ያመጣውን ግሩም ለውጥ በማየቱ በጣም ተገርሟል

የክሱ ሂደት

ነሐሴ 19, 2018 ፖሊሶች በየሊዞቮ ከተማ የሚገኙ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶች በረበሩ። አሥራ አንድ ወንድሞችና እህቶች ታሰሩ። ከዚያም ለበርካታ ሰዓታት ምርመራ ሲደረግባቸው ቆየ። በኋላም ስምንቱ የይሖዋ ምሥክሮች ተለቀቁ። ሆኖም ፖሊሶች በወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ፣ በባለቤቱና በእህት ቬራ ዞሎቶቫ ላይ ክስ መሠረቱ። እነዚህ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ተደረገ። ከሁለት ቀን በኋላ እህቶች ተለቀቁ። ሆኖም ዳኛው ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭ በእስር እንዲቆይ አዘዙ። ከስምንት ቀን በኋላ እሱም ተለቀቀ።

ወንድም ኮንስታንቲን ባዠኖቭና ባለቤቱ እንዲሁም እህት ቬራ ዞሎቶቫ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በሚጠባበቁበት ወቅት በይሖዋ ሙሉ በሙሉ መተማመናቸውን እንዲቀጥሉ እንጸልያለን። መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ ታማኞቹን ደስታና ሰላም እንደሚሞላባቸው እንዲሁም “በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተስፋ” እንደሚትረፈረፍላቸው ዋስትና ይሰጠናል።—ሮም 15:13

a ቀኑ ሊቀየር ይችላል