በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 9, 2020
ሩሲያ

ሩሲያ ውስጥ ወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ የስድስት ዓመት ተኩል እስር ተፈረደበት

ሩሲያ ውስጥ ወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ የስድስት ዓመት ተኩል እስር ተፈረደበት

ማክሰኞ ሰኔ 9, 2020 የፓስኮቭ ከተማ ፍርድ ቤት በ61 ዓመቱ በወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ ላይ የስድስት ዓመት ተኩል እስር በይኗል። ወንድም ጀናዲ ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወደ እስር ቤት ተወስዷል። ይህ ውሳኔ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምናደርገውን እንቅስቃሴ ከወንጀል ድርጊቶች ከፈረጀበት ከ2017 በኋላ በወንድሞቻችን ላይ የተበየነው ረጅሙ እስራት ነው። ወንድም ጀናዲ ሽፓኮቭስኪ የተላለፈበትን ፍርድ አስመልክቶ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ታውቋል።