በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የላይኛው መደዳ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ኬቶቭ፣ ወንድም አንድሬ ኻርላሞቭ እና ባለቤቱ ላሪሳ፣ ወንድም አሌክሳንደር ክሩግሊያኮቭ

የታችኛው መደዳ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ሊዲያ ኒክራሶቫ፣ ወንድም ሰርጌ ኡሻኺን

ነሐሴ 10, 2023
ሩሲያ

ስደት እየደረሰባቸውም ደስተኞች ሆነው ቀጥለዋል

ስደት እየደረሰባቸውም ደስተኞች ሆነው ቀጥለዋል

በኮሚ ሪፑብሊክ የሚገኘው የሲክቲቭካርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በወንድም አሌክሳንደር ኬቶቭ፣ በወንድም አንድሬ ኻርላሞቭ፣ በወንድም አሌክሳንደር ክሩግሊያኮቭ፣ በእህት ሊዲያ ኒክራሶቫ እና በወንድም ሰርጌ ኡሻኺን ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

ከእነዚህ ተሞክሮዎች እንደምንረዳው ይሖዋ መከራን በጽናት እየተቋቋሙ ላሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን “የተሟላ ብርታት” በመስጠት ታማኝ ሆነው እንዲቀጥሉ እየረዳቸው ነው።—ኢሳይያስ 40:29

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 2, 2021

    በሲክቲቭካር ቢያንስ 14 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። አሌክሳንደር ኬቶቭ፣ አንድሬ ኻርላሞቭ እና አሌክሳንደር ክሩግሊያኮቭ በጊዜያዊ ማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ተደረገ። ሊዲያ ኒክራሶቫ እና ሰርጌ ኡሻኺን ደግሞ የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው

  2. መጋቢት 3, 2021

    አሌክሳንደር ኬቶቭ እና አንድሬ ኻርላሞቭ ከማረፊያ ቤት ወጥተው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረገ። አሌክሳንደር ክሩግሊያኮቭ ወደ ማረፊያ ቤት ተላከ

  3. ሚያዝያ 27, 2021

    አንድሬ ኻርላሞቭ ከቁም እስር ተለቀቀ

  4. ሚያዝያ 28, 2021

    አሌክሳንደር ኬቶቭ ከቁም እስር፣ አሌክሳንደር ክሩግሊያኮቭ ደግሞ ከማረፊያ ቤት ተለቀቁ

  5. ሚያዝያ 19, 2022

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  6. ሰኔ 9, 2022

    ዳኛው ጽንፈኝነትን የሚያሳይ በቂ ማስረጃ አለማግኘታቸውን በመግለጽ ክሱን ወደ አቃቤ ሕጉ መለሱት

  7. የካቲት 14, 2023

    አዲስ ዳኛ ተመድቦ ክሳቸው በድጋሚ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ