ሰኔ 28, 2024
ሩሲያ
በሩሲያ፣ ካልሚኪያ ሪፑብሊክ የሚኖሩ ሦስት እህቶች ተፈረደባቸው
ሰኔ 24, 2024 በካልሚኪያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የኤሊስታ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በእህት ሳጋን ሃልጋዬቫ፣ በእህት ዬካተሪና ሜንኮቫ እና በእህት ኪሽታ ቱቲኖቫ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሳጋን እና ዬካተሪና እያንዳንዳቸው የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። ኪሽታ ደግሞ የሦስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
አጭር መግለጫ
እንዲህ ያሉ ዘመናዊ የእምነት ምሳሌዎችን እናደንቃለን። ይሖዋ የምናልፍበትን መከራ ሁሉ እንደሚመለከትና ለታማኝነታችን ወሮታ እንደሚከፍለን ስለምናውቅ አመስጋኞች ነን።—መዝሙር 37:18
የክሱ ሂደት
የካቲት 16, 2023
ኪሽታ የክስ ፋይል ተከፈተባት
የካቲት 28, 2023
ቤታቸው ተፈተሸ። ኪሽታ ጣቢያ ተወሰደች
መጋቢት 1, 2023
ሳጋን በከባድ ወንጀል በመጠርጠሯ ከሥራዋ ተባረረች። ኪሽታ ከጣቢያ ተለቅቃ የቁም እስረኛ ሆነች
ሐምሌ 21, 2023
ኪሽታ ከቁም እስር ተፈታች
ታኅሣሥ 19, 2023
ዬካተሪና እና ሳጋን የክስ ፋይል ተከፈተባቸው። ሁለቱም የጉዞ ገደቦች ተጣሉባቸው
የካቲት 9, 2024
ኪሽታ የጉዞ ገደቦች ተጣሉባት
ሚያዝያ 1, 2024
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ሰኔ 24, 2024
ጥፋተኛ ተብለው የገደብ እስራት ተፈረደባቸው