ጥር 20, 2022
ሩሲያ
በሩሲያ የሚኖሩ ሰባት ወንድሞች ከፈጣሪያቸው ብርታት አግኝተዋል
በኮሚ ሪፑብሊክ የሚገኘው የፔቾራ ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም ኒኮላይ አኑፍሪዬቭ፣ በወንድም ኤዱዋርድ ሜሪንኮቭ፣ በወንድም ጀናዲ ፖልያኬቪች፣ በወንድም አሌክሳንደር ፕሪሌፕስኪ፣ በወንድም ቪክቶር ሽቻኒኮቭ፣ በወንድም ጀናዲ ስኩቴሌትስ እና በወንድም አሌክሳንደር ቮሮንትሶቭ ላይ የተመሠረተውን ክስ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔውን ያሳልፋል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
የክሱ ሂደት
ጥር 28, 2020
ባለሥልጣናቱ በኮሚ ሪፑብሊክ የሚኖሩ 12 ቤተሰቦችን ቤቶች በረበሩ። በወንድም ፖልያኬቪች እና በወንድም ስኩቴሌትስ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተ
ጥር 30, 2020
ጀናዲ ፖልያኬቪች ማረፊያ ቤት ገባ፤ ጀናዲ ስኩቴሌትስ ደግሞ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ግንቦት 20-25, 2020
በፔቾራ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች ለክሱ ምሥክሮች እንደሚሆኑ በማሰብ ፖሊስ ምርመራ አደረገባቸው። አንድ ወንድም፣ መርማሪው ካስፈራራው በኋላ ስትሮክ መታው። እርግጥ አሁን ጤንነቱ ተሻሽሏል
ሰኔ 26, 2020
የጀናዲ ፖልያኬቪች የማረፊያ ቤት ቆይታ እንዲራዘም ተደረገ። ዳኛው ጀናዲ ፖልያኬቪች የተከሰሰው “ሆን ብሎ ከባድ ወንጀል” በመሥራት እንደሆነ ገለጹ፤ ይህም “ባለሥልጣናት ስደት ቢያደርሱም ይሖዋን ማገልገልን ስለመቀጠል” መናገርን ይጨምራል
ነሐሴ 24, 2020
ባለሥልጣናት የሌሎች 12 የይሖዋ ምሥክር ቤተሰቦችን መኖሪያዎች በረበሩ
ኅዳር 10, 2020
በአሌክሳንደር ፕሪሌፕስኪ፣ በአሌክሳንደር ቮሮንትሶቭ፣ በኤዱዋርድ፣ በኒኮላይ እና በቪክቶር ላይ የወንጀል ክስ ተከፈተ። ጉዳያቸው ከጀናዲ ፖልያኬቪች እና ከጀናዲ ስኩቴሌትስ ጉዳይ ጋር አብሮ መታየት ጀመረ
ኅዳር 25, 2020
ጀናዲ ፖልያኬቪች ለ300 ቀናት በማረፊያ ቤት ከቆየ በኋላ ተለቆ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ
ጥር 27, 2021
ጀናዲ ስኩቴሌትስ ለ363 ቀናት በቁም እስር ከቆየ በኋላ ተለቀቀ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችን በይሖዋ ጥሩነት ላይ እምነት በማሳደራቸው አሁንም ሆነ ወደፊት እንደሚባረኩ እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 27:13