በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ሰርጌ ሬይማን እና ባለቤቱ ቫሌሪያ

መስከረም 7, 2020
ሩሲያ

በሩሲያ የሚኖሩ ወጣት ባልና ሚስት ፍርድ ይጠብቃቸዋል

በሩሲያ የሚኖሩ ወጣት ባልና ሚስት ፍርድ ይጠብቃቸዋል

የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን

መስከረም 16, 2020 a በኮስትሮማ ከተማ የሚገኘው የስቬርድሎቭስኪ የአውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም ሰርጌ ሬይማን እና በባለቤቱ በቫሌሪያ ላይ ከተመሠረተው ክስ ጋር በተያያዘ ውሳኔውን እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። ሁለቱም የሰባት ዓመት እስር በገደብ ሊፈረድባቸው ይችላል።

አጭር መግለጫ

ሰርጌ ሬይማን

  • የትውልድ ዘመን፦ 1996 (ኪኔሽማ፣ ኢቫኖቮ ክልል)

  • ግለ ታሪክ፦ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት የግንባታ ሙያ ተምሯል። በዋነኝነት የሚሠራው የቤት ውስጥ ዲዛይን ነው። ለመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅርና አድናቆት እንዲያድርበት የረዱት ሴት አያቱ ናቸው። በ2015 ቫሌሪያን አገባ። ምግብ ማብሰልና የበረዶ ላይ ሸርታቴ ያስደስተዋል

ቫሌሪያ ሬይማን

  • የትውልድ ዘመን፦ 1993 (ሻርያ፣ ኮስትሮማ ክልል)

  • ግለ ታሪክ፦ የአሥር ዓመት ልጅ እያለች አባቷ ሞተ። ስለ ይሖዋ የተማረችው ከእናቷ ነው። ፈቃድ ያላት የፀጉር ሥራ ባለሙያ ነች

የክሱ ሂደት

ሐምሌ 25, 2018 ማለዳ ላይ መሣሪያ የታጠቁ ልዩ ኃይሎች የብረት መፈልቀቂያ በመጠቀም የእነ ወንድም ሰርጌን ቤት ሰብረው ገቡ። ፖሊሶቹ ባልና ሚስቱን በቁጥጥር ሥር አዋሏቸው። እህት ቫሌሪያ ለሁለት ቀናት በማረፊያ ቤት ቆየች። ወንድም ሰርጌ ደግሞ ለ59 ቀናት ብቻውን ታስሮ ነበር። ባለሥልጣናቱ እነ ወንድም ሰርጌ ከሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ ገደብ ጥለዋል። በተጨማሪም ከመሸ በኋላ ከቤታቸው መውጣት አይችሉም። ይህ ሁኔታ ከፍተኛ ውጥረት የፈጠረባቸው ከመሆኑም ሌላ በአካላዊም ሆነ በስሜታዊ ጤንነታቸው ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

እነዚህ ወጣት ባልና ሚስት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በሚጠባበቁበት ወቅት ደፋርና ብርቱ ሆነው እንዲቀጥሉ ጸሎታችን ነው፤ ይሖዋ ምንጊዜም እንደሚደግፋቸው እንተማመናለን።—ኢያሱ 1:9

a ቀኑ ሊቀየር ይችላል