ኅዳር 29, 2023
ሩሲያ
በሩሲያ ያለው የሳራቶቭ ክልል ፍርድ ቤት አምስት ወንድሞች ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላለፈ
ኅዳር 23, 2023 በሳራቶቭ ክልል የሚገኘው የባላኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት በወንድም አሌክሲ ቦጋቶቭ፣ በወንድም ዬቭጌኒ ፎማሺን፣ በወንድም ቭላዲሚር ማቭሪን፣ በወንድም አንድሬ ሙሪክ እና በወንድም ሰርጌ ትዩሪን ላይ ከተመሠረተው ክስ ጋር በተያያዘ ውሳኔውን አሳውቋል። አምስቱም ወንድሞች ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን ተላልፎባቸዋል። አሌክሲ እና ቭላዲሚር የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። አንድሬ፣ ሰርጌ እና ዬቭጌኒ ደግሞ እያንዳንዳቸው 300,000 ሩብል (3,362 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ እንዲከፍሉ ተወስኗል። ሁሉም ወንድሞች በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
አጭር መግለጫ
የእነዚህ አምስት ታማኝ ወንድሞች ምሳሌ ይሖዋ በሚሰጠው ኃይል እስከታመንን ድረስ በምሥራቹ ምክንያት የሚደርስብንን መከራ መቋቋም እንደምንችል ያሳያል።—2 ጢሞቴዎስ 1:8
የክሱ ሂደት
የካቲት 11, 2022
የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው
መጋቢት 23, 2022
የፌዴራል ደህንነት አባላት የአምስቱንም ወንድሞች ቤቶች ፈተሹ። እያንዳንዳቸው ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ተወሰዱ
መጋቢት 25, 2022
ወንድሞች ማረፊያ ቤት ገቡ
ጥር 23, 2023
ወንድሞች ከእስር ተለቀው የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው
ሐምሌ 21, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
ኅዳር 23, 2023
ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ተፈረደባቸው