በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከላይ፣ ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ዬቭጌኒ ጎዱኖቭ እና ወንድም ጉራሚ ላባድዜ

ከታች፣ ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ዩልያ ፖፕኮቫ እና እህት አንጂላ ፑቲቭስካያ

ኅዳር 21, 2023
ሩሲያ

በቱላ፣ ሩሲያ ያሉ አራት የይሖዋ ምሥክሮች የገደብ እስራት ተፈረደባቸው

በቱላ፣ ሩሲያ ያሉ አራት የይሖዋ ምሥክሮች የገደብ እስራት ተፈረደባቸው

ኅዳር 20, 2023 በቱላ የሚገኘው የፕሮሌታርስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ዬቭጌኒ ጎዱኖቭ፣ ወንድም ጉራሚ ላባድዜ፣ እህት ዩልያ ፖፕኮቫ እና እህት አንጂላ ፑቲቭስካያ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ወንድም ዬቭጌኒ እና ወንድም ጉራሚ የስድስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። እህት ዩልያ እና እህት አንጂላ ደግሞ የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

የእነዚህ ወንድሞችና እህቶች ምሳሌ እኛም በይሖዋ ከታመንን እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የእምነት ምሳሌዎች ለመከተል ጥረት ካደረግን ማጽናኛና ተስፋ ማግኘት እንደምንችል ያረጋግጡልናል።—ሮም 15:4

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 25, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  2. ሚያዝያ 13, 2021

    ቤታቸው ተፈተሸ። አንጂላ እና ዩልያ ታሰሩ

  3. ሚያዝያ 14, 2021

    አንጂላ እና ዩልያ ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰዱ። ዬቭጌኒ የታሰረ ሲሆን ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ተላለፈበት። ጉራሚ በቁም እስር እንዲቆይ ተደረገ

  4. ሚያዝያ 16, 2021

    ዬቭጌኒ ወደ ማረፊያ ቤት ተወሰደ

  5. ግንቦት 20, 2021

    አንጂላ፣ ዬቭጌኒ እና ዩልያ ከማረፊያ ቤት ወጥተው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረጉ

  6. ሐምሌ 22, 2021

    አንጂላ፣ ዬቭጌኒ እና ዩልያ ከቁም እስር ተለቀው የጉዞ ገደብ ተጣለባቸው

  7. ሐምሌ 23, 2021

    ጉራሚ ከቁም እስር ተለቆ የጉዞ ገደብ ተጣለበት

  8. ግንቦት 11, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  9. ኅዳር 20, 2023

    ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን ተላልፎባቸው የገደብ እስራት ተፈረደባቸው