በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ እህት ዳርያ ዱሎቫ እና እህት ቨነራ ዱሎቫ። በስተ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ፕሪያኒኮቭ እና ባለቤቱ አናስታሲያ። መሃል፦ እህት ስቬትላና ዛልያዬቫ

ጥር 20, 2022
ሩሲያ

በካርፒንስክ ከተማ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በይሖዋ መታመናቸውንና እምነታቸውን ማጠናከራቸውን ቀጥለዋል

በካርፒንስክ ከተማ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በይሖዋ መታመናቸውንና እምነታቸውን ማጠናከራቸውን ቀጥለዋል

በስቬርድሎቭስክ ክልል የሚገኘው የካርፒንስኪ ከተማ ፍርድ ቤት የእህት ዳርያ ዱሎቫን፣ የእህት ቨነራ ዱሎቫን፣ የወንድም አሌክሳንደር ፕሪያኒኮቭን እና የእህት አናስታሲያ ፕሪያኒኮቫን እንዲሁም የእህት ስቬትላና ዛልያዬቫን ጉዳይ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔውን ያሳልፋል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም

የክሱ ሂደት

  1. ጥር 27, 2020

    አሌክሳንደር፣ ዳርያ እና ቨነራ በተመሠረተባቸው ሌላ ክስ ፍርድ ተላለፈባቸው

  2. የካቲት 2020

    በአሌክሳንደር፣ በዳርያ እና በቨነራ ላይ ሁለተኛ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  3. መጋቢት 30, 2020

    ባለሥልጣናት ክስ የተመሠረተባቸውን የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች በረበሩ፤ እንዲሁም የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻቸውን ወረሱ

  4. ግንቦት 19, 2020

    አናስታሲያ እና ስቬትላና በወንጀል ክሱ ውስጥ ተካተቱ። ሁለቱም አካባቢያቸውን ለቀው እንዳይሄዱ ታዘዙ

  5. ሚያዝያ 29, 2021

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ሩሲያ ውስጥ በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የሚደርሰው ስደት ቢቀጥልም ይሖዋ እነዚህን ውድ ክርስቲያኖች በፍቅር መንከባከቡንና መደገፉን እንደቀጠለ ማየት ምንኛ እምነት የሚያጠናክር ነው! ተፈትኖ የተረጋገጠው እምነታቸው ለይሖዋ ስም “ምስጋናን፣ ግርማንና ክብርን” እያስገኘ ነው።—1 ጴጥሮስ 1:7