ሐምሌ 10, 2023
ሩሲያ
በኮምሶሞልስክ ና አሙሪ ሦስት እህቶች ተፈረደባቸው
መጋቢት 23, 2023 በኮምሶሞልስክ ና አሙሪ የሚገኘው የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ታትያና ቦንዳሬንኮ፣ እህት ዬሌና ኔስቴሮቫ እና እህት ታትያና ስቮቦዳ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ውሳኔ አስተላለፈ። እያንዳንዳቸው የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ፣ መከራን ተቋቁመው ታማኝነታቸውን የጠበቁትን እህቶቻችንን እንዲባርካቸውና እንዲያበረታቸው እንጸልያለን።—ሩት 2:12
የክሱ ሂደት
መስከረም 21, 2021
ታትያና ስቮቦዳ የክስ ፋይል ተከፈተባት
ጥቅምት 18, 2021
ታትያና ቦንዳሬንኮ እና ዬሌና ኔስቴሮቫ በክስ ፋይሉ ውስጥ ተካተቱ
ጥቅምት 20, 2021
ቤታቸው ተፈተሸ
ነሐሴ 28, 2022
ክስ ተመሠረተባቸው
ታኅሣሥ 28, 2022
የወንጀል ክሶቹ በፍርድ ቤት መታየት ጀመሩ
መጋቢት 23, 2023
ጥፋተኞች ናቸው የሚል ብያኔ ተሰጠ፤ እንዲሁም እያንዳንዳቸው የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባቸው