በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን በ2018 በፍርድ ቤቱ የእስረኞች ማቆያ ክፍል ውስጥ ሆኖ

ሐምሌ 8, 2020
ሩሲያ

በወንድም ክሪስተንሰን ላይ ይተላለፋል የተባለው ቅጣት ሌሎች የሐሰት ክሶች በመቅረባቸው ምክንያት ለአምስት ቀናት ተራዘመ

በወንድም ክሪስተንሰን ላይ ይተላለፋል የተባለው ቅጣት ሌሎች የሐሰት ክሶች በመቅረባቸው ምክንያት ለአምስት ቀናት ተራዘመ

ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ለቅጣት ከታሰረበት ክፍል a ይወጣል የተባለው ሐምሌ 6, 2020 ነበር። ሆኖም በዚያው ቀን የልጎፍ እስር ቤት አርፋጅነትን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ቢስ ክሶችን እንደ ምክንያት በመጥቀስ ወንድም ክሪስተንሰን በዚያ ክፍል ውስጥ ለአምስት ተጨማሪ ቀናት እንዲቆይ አድርጓል።

ባለሥልጣናቱ ቀደም ብሎ ለመፈታት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንዲሆን ስለፈለጉ ሆን ብለው እየዋሹ እንደሆነ ወንድም ክሪስተንሰን ለጠበቃው ነግሮታል። ከአንድ ዓመት ከሚበልጥ ጊዜ በፊት ወንድም ክሪስተንሰን ከተፈረደበት የስድስት ዓመት እስር ውስጥ የተወሰነውን በእስር እንዳሳለፈ ይታወሳል፤ በእስር ያሳለፈው ጊዜ ቀደም ብሎ የመፈታት ጥያቄ ለማቅረብ ብቁ እንዲሆን ያደርገዋል። ሆኖም አራት ጊዜ ማመልከቻ ቢያስገባም የልጎፍ ፍርድ ቤትና የእስር ቤት ጠባቂዎች ጥያቄው ተቀባይነት እንዳያገኝ እያደረጉ ነው።

የሩሲያ ባለሥልጣናት የውድ ወንድሞቻችንን ስም ማጉደፋቸውን ቀጥለዋል፤ ሆኖም ይሖዋ ሰላም በመስጠትና ‘ሞገሱ እንደ ትልቅ ጋሻ እንዲሆንላቸው’ በማድረግ ወንድሞቻችንን እንደሚረዳቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 5:12፤ 119:69

a ቀደም ሲል ባወጣነው ሪፖርት ላይ ወንድም ክሪስተንሰን ከእስር ጊዜው ቀደም ብሎ እንዲፈታ በፍርድ ቤት ከተወሰነ ብዙም ሳይቆይ ውሳኔው ለይግባኝ እንደቀረበና ወንድም ክሪስተንሰን ወደ ልዩ የቅጣት ክፍል እንደተላከ ሪፖርት አድርገን ነበር፤ በተጨማሪም ይህ የቅጣት ክፍል በጣም አስቸጋሪ ወንጀለኞች የሚታሰሩበት እንደሆነ ገልጸን ነበር። ሆኖም ይህ የቅጣት ክፍል በሚገኝበት ሕንፃ ውስጥ ሺዞ የተባለ አነስተኛ ጥፋት የሠሩ ሰዎች የሚቆዩበት ሌላ የቅጣት ክፍል አለ። አሁን ባለን መረጃ መሠረት ወንድም ክሪስተንሰን የተወሰደው ወደ ሺዞ የቅጣት ክፍል ነው።