በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኦሌግ ሲሮትኪን

ታኅሣሥ 2, 2022
ሩሲያ

“በጣም አስፈላጊ ነገር እያከናወንኩ ነው”

“በጣም አስፈላጊ ነገር እያከናወንኩ ነው”

በታምቦቭ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ የወንድም ኦሌግ ሲሮትኪንን ጉዳይ ተመልክቶ በቅርቡ ብይን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

የኦሌግ ምሳሌ አንድ ቁም ነገር ያስታውሰናል፤ በይሖዋ ላይ ጠንካራ እምነት ያለው ሰው “ክፉ ወሬ አያስፈራውም። በይሖዋ ስለሚተማመን ልቡ ጽኑ ነው።”—መዝሙር 112:7

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 2021

    ፖሊሶች በድብቅ ይከታተሉት ጀመር። ሳሎኑ ውስጥ የድምፅ መቅጃ በድብቅ ተከሉ፤ ኮምፒውተሩ ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴም ፎቶ አነሱ

  2. መስከረም 14, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. መስከረም 21, 2021

    ቤቱ ተፈተሸ። ኮምፒውተሩና የግል ፋይሎቹ ለክሱ ማስረጃ ይሆናሉ በሚል ተወረሱበት

  4. ጥቅምት 22, 2021

    መኪናው ተወረሰች

  5. ሚያዝያ 11, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ