በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ገሊና ፓርኮቫ

ጥር 25, 2021
ሩሲያ

ባለቤቷ በእስር ላይ ያለው እህት ገሊና ፓርኮቫ በእምነቷ ምክንያት ክስ ቀርቦባት ፍርድ እየተጠባበቀች ነው

ባለቤቷ በእስር ላይ ያለው እህት ገሊና ፓርኮቫ በእምነቷ ምክንያት ክስ ቀርቦባት ፍርድ እየተጠባበቀች ነው

የፍርድ ውሳኔ የሚሰጥበት ቀን

በሮስቶቭ-ኦን-ዶን ከተማ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት የእህት ገሊና ፓርኮቫን ጉዳይ ተመልክቶ በቅርቡ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። a እህት ገሊና ጥፋተኛ ሆና ከተገኘች በሦስት ዓመት የገደብ እስራት እንድትቀጣ አቃቤ ሕጉ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

አጭር መግለጫ

ገሊና ፓርኮቫ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1970 (ካልታን)

  • ግለ ታሪክ፦ በ1990 ገሊና ከአሌክሳንደር ጋር ትዳር መሠረተች። ሦስት ሴቶች ልጆችና ሁለት የልጅ ልጆች አሏቸው። ባልና ሚስቱ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን አጠኑ። ገሊና በ1995 ተጠመቀች። መዝፈንና ሥዕል መሣል ትወዳለች

የክሱ ሂደት

ባለሥልጣናቱ ሰኔ 6, 2019 በገሊና ላይ የወንጀል ክስ መሠረቱ። ይህ ከመሆኑ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባለቤቷ አሌክሳንደር የተያዘ ሲሆን ችሎት ፊት እስኪቀርብ ድረስ እስር ላይ ይገኛል።

ገሊና ባለቤቷ ከታሰረ ወዲህ ኑሮ ከባድ ሆኖባታል። በተጨማሪም ባለሥልጣናቱ የባንክ ሒሳቧን ስላገዱባት ደሞዟን ጨምሮ በባንክ ያላትን ገንዘብ መጠቀም አልቻለችም። በመሆኑም ራሷን ለማስተዳደር ስትል ቀደም ሲል የነበራትን ሥራ ለቅቃ ያገኘችውን ማንኛውንም ሥራ ለመሥራት ተገድዳለች።

በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን “ክፉ እንደሠሩ ተደርገው የሚታዩ ጻድቃን” ናቸው። (መክብብ 8:14) ያም ቢሆን የእነሱ የእምነት ምሳሌ እኛም ማንኛውም ዓይነት መከራ ቢያጋጥመን እንድንጸና ያበረታናል።

a ፍርድ ቤቱ ብይን የሚያስተላልፍበትን ቀን አስቀድሞ የማያሳውቅበት ጊዜ አለ