በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ ከእስር ቤት ተፈትቶ ከባለቤቱ ከዞያ እና ከልጃቸው ጋር ሲገናኝ። ውስጠኛው፦ ቫሲሊ እና ዞያ

ሐምሌ 16, 2024
ሩሲያ

ቫሲሊ ሜሌሽኮ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ

ቫሲሊ ሜሌሽኮ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ

ሐምሌ 12, 2024 ወንድም ቫሲሊ ሜሌሽኮ ከእስር ቤት ተፈትቷል። በ2021 ጥፋተኛ ነው የሚል ፍርድ ተበይኖበት የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት ነበር

ቫሲሊ በእስር ላይ እያለ ቢያንስ ወደ ሰባት የተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ተዘዋውሯል። በአንድ ወቅት የቫሲሊ ባለቤት ዞያ፣ ባለቤቷ የት እንዳለ ለአንድ ወር ገደማ አልተነገራትም ነበር። ቫሲሊ የጤና እክሎች ስላሉበት በዚህ ጊዜ በጣም ተጨንቃ ነበር።

ዞያ፣ እሷና ቫሲሊ መለያየታቸው ያስከተለባቸውን ጫና ለመቋቋም ምን እንደረዳቸው ስትገልጽ እንዲህ ብላለች፦ “ይህ ሁኔታ ትዳራችንን እንዲያናጋውና በመንፈሳዊ እንዲያዳክመን ብንፈቅድ ሰይጣን በጣም እንደሚደሰት እናውቃለን። ስለዚህ እኔና ቫሲሊ እርስ በርሳችንም ሆነ ከይሖዋ ጋር ያለን ግንኙነት ምንጊዜም ጠንካራና የማይናወጥ ሆኖ እንዲቀጥል የምንችለውን ሁሉ እናደርግ ነበር። ቫሲሊ እንደሚወደኝ የሚያረጋግጡልኝ ግሩም ደብዳቤዎች ይልክልኝ እንዲሁም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በመንፈሳዊ ያበረታታኝ ነበር።”

ቫሲሊ ከዞያ እና ከወዳጅ ቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀል በመቻሉ ደስ ብሎናል። በእምነታቸው ምክንያት ለታሰሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መጸለያችንን እንቀጥላለን፤ ይሖዋም በመከራችን ሁሉ እንደሚደግፈን እንተማመናለን።​—መዝሙር 55:22