በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሩሲያ በእምነታቸው ምክንያት ወንጀለኛ ተብለው የተፈረደባቸው ከ60 ዓመት በላይ ዕድሜ ያላቸው ወንድሞችና እህቶች

ነሐሴ 2, 2021
ሩሲያ

ታማኝ አረጋውያን ስደት ቢደርስባቸውም ደስታቸውን ጠብቀዋል

ታማኝ አረጋውያን ስደት ቢደርስባቸውም ደስታቸውን ጠብቀዋል

በ2017 በሩሲያ በይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ ማዕከላት ላይ እገዳ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ባለሥልጣናቱ በመላዋ አገሪቱ በሚገኙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ ያለአግባብ ጥቃት እየሰነዘሩ ነው፤ እስካሁን ጥቃት የተሰነዘረባቸው ወንድሞቻችን ከ18 እስከ 89 ባለው ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። እስከ ሐምሌ 2021 ድረስ ዕድሜያቸው 60 እና ከዚያ በላይ የሆነ 18 ወንድሞችና እህቶች በሰላማዊ መንገድ አምልኳቸውን በማከናወናቸው ምክንያት ብቻ ወንጀለኛ ተብለው ቅጣት ተበይኖባቸዋል። ከእነዚህ መካከል ሦስቱ በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ይገኛሉ። a የ2021 የበላይ አካሉ ሪፖርት ቁጥር 4 በአረጋውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ላይ እየተፈጸመ ስላለው አሰቃቂ ጥቃት ገልጾ ነበር።

ውድ አረጋውያን ወንድሞቻችን የሚደርስባቸውን ስደት የተቋቋሙት እንዴት ነው? አንዳንዶቹ የሰጧቸውን አበረታች ሐሳቦች ስናካፍላችሁ ደስ ይለናል።

በሩሲያ ያሉ ታማኝ አረጋውያን ለተዉት መልካም ምሳሌ አመስጋኞች ነን። ከጽድቅ ጎን ለመቆም የወሰዱት የድፍረት አቋም ሊኮረጅ የሚገባው ነው፤ ይህ አቋማቸው በይሖዋ ዓይን ውብ ነው።—ምሳሌ 16:31

a የ70 ዓመቷ እህት ቫለንቲና ባራኖቭስካያ የሁለት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም የ63 ዓመቱ አሌክሳንደር ኢቨሺን የሰባት ዓመት ተኩል እስራት፣ የ68 ዓመቱ ወንድም ዩሪ ሳቨላየቭ ደግሞ የስድስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ።