በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሩሲያ

ታሪካዊ እመርታዎች በሩሲያ

ታሪካዊ እመርታዎች በሩሲያ
  1. ግንቦት 5, 2018—የሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ፍርድ ቤት፣ መንግሥት በሩሲያ ያለውን የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር ማዕከል እንዲወርስ የተላለፈውን ብይን አጸደቀ

    ተጨማሪ መረጃ

  2. ሐምሌ 17, 2017—የሩሲያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሚያዝያ 20 ላይ የተላለፈውን ብይን አጸደቀ። በሩሲያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ታገደ

    ተጨማሪ መረጃ

  3. ሚያዝያ 20, 2017—የሩሲያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሩሲያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ እንደ ወንጀል እንዲቆጠር ውሳኔ አስተላለፈ

    ተጨማሪ መረጃ

  4. ኅዳር 30, 2015—በታጋንሮግ ጉዳያቸው በድጋሚ እየታየላቸው የነበሩት 16ቱም የይሖዋ ምሥክሮች አምልኳቸውን በማካሄዳቸው ወንጀለኛ ናቸው ተብሎ ተፈረደባቸው። ዳኛው በእስራት እንዳይቀጡ ወሰኑ

    ተጨማሪ መረጃ

  5. ታኅሣሥ 2, 2014—የሩሲያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ፍርድ ቤት jw.org​ን አገደ

    ተጨማሪ መረጃ

  6. ሐምሌ 30, 2014—በታጋንሮግ ጉዳያቸው እየታየ ከነበሩት 16 የይሖዋ ምሥክሮች መካከል ሰባቱ አምልኳቸውን በማካሄዳቸው ወንጀለኛ ናቸው ተብሎ ተፈረደባቸው

    ተጨማሪ መረጃ

  7. ሰኔ 10, 2010—የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት በሞስኮ ባሉ የይሖዋ ምሥክሮች ላይ የተጣለው እገዳ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሆነ ገለጸ

  8. መስከረም 11, 2009—የሮስቶቭ ክልላዊ ፍርድ ቤት 34 የይሖዋ ምሥክሮች ጽሑፎች ጽንፈኛ ናቸው ብሎ ፈረጀ

  9. 2009—የሩሲያ ሕግ አስከባሪ አካላት የጽንፈኝነት እንቅስቃሴን ለመከላከል ሲባል የወጣውን የፌዴራል ሕግ በተሳሳተ መንገድ መጠቀም ጀመሩ

  10. መጋቢት 26, 2004—በሞስኮ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ታገደ

  11. መጋቢት 1996—የይሖዋ ምሥክሮች የፖለቲካዊ ጭቆና ሰለባ የሆኑ ንጹሐን ዜጎች እንደሆኑ ተገለጸ

  12. ታኅሣሥ 11, 1992—የይሖዋ ምሥክሮች በሩሲያ ፌዴሬሽን ሕጋዊ እውቅና ተሰጥቷቸው ተመዘገቡ

  13. መጋቢት 27, 1991—የይሖዋ ምሥክሮች በሶቪየት ኅብረት ሕጋዊ እውቅና አግኝተው ተመዘገቡ

  14. ጥቅምት 1965—መንግሥት የጣላቸው እገዳዎች እንዲሁም በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የሚፈጸመው ጭቆና ጋብ አለ

  15. ሚያዝያ 1951—በስድስት የሶቪየት ሪፑብሊኮች የሚኖሩ 9,500 ገደማ የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች ወደ ሳይቤሪያ በግዞት ተወሰዱ

  16. 1928—የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ እውቅና ማግኘት አልቻሉም፤ ለዓመታት የዘለቀው ስደት ጀመረ

  17. 1891—የመጀመሪያው ሩሲያዊ የይሖዋ ምሥክር ወደ ሳይቤሪያ በግዞት ተወሰደ

  18. 1887—መረጃዎች እንደሚያሳዩት መጠበቂያ ግንብ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩሲያ በፖስታ የተላከው በዚህ ዓመት ነው