በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ፓርኮቭ ከእስር ቤት በወጣበት ወቅት ባለቤቱ ገሊና ስትቀበለው

ነሐሴ 13, 2024
ሩሲያ

አሌክሳንደር ፓርኮቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ

አሌክሳንደር ፓርኮቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቀቀ

ነሐሴ 9, 2024 ወንድም አሌክሳንደር ፓርኮቭ ከሩሲያ ወህኒ ቤት ተለቅቋል። ሐምሌ 29, 2021 አሌክሳንደር የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈርዶበት ነበር። ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን ከመተላለፉ በፊት ማረፊያ ቤት ያሳለፈው ጊዜ ታሳቢ ስለተደረገ የእስራት ጊዜው ተጠናቅቋል።

አሌክሳንደርና ባለቤቱ እህት ገሊና ፓርኮቫ ከአምስት ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ ተለያይተው ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ገሊና፣ ሌላ የክስ ፋይል ተከፍቶባት የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። ከዚህም ሌላ በዚህ ክስ ምክንያት ሥራዋን አጥታለች።

አሌክሳንደር በእስር ላይ እያለ ሚስቱን በስልክ ማነጋገርና ከእሷ ጋር ደብዳቤ መጻጻፍ ተፈቅዶለት ነበር። ገሊና በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ባለቤቷ እንዴት ያበረታታት እንደነበር በማስታወስ እንዲህ ብላለች፦ “ይሖዋ ከእኛ ጋር እስከሆነ ድረስ ምንም የሚያስፈራን ነገር እንደሌለ ደጋግሞ ያስታውሰኝ ነበር።”

አሌክሳንደርና ገሊና አብረው ሆነው ይሖዋን በአንድነት ማምለካቸውን ሲቀጥሉ የይሖዋ በረከት እንደማይለያቸው እርግጠኞች ነን። እኛም “በጸሎት ረገድ ንቁዎች” በመሆን በእምነታቸው ምክንያት እስር ቤት ያሉትን ሁሉ እናስባቸዋለን።​—1 ጴጥሮስ 4:7