በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 30, 2020
ሩሲያ

አቃቤ ሕግ ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የተላለፈውን ውሳኔ ይግባኝ አለ

አቃቤ ሕግ ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የተላለፈውን ውሳኔ ይግባኝ አለ

የኩርስክ ክልል አቃቤ ሕግ የሆነው ሻቱኖቭ፣ ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን የእስር ጊዜውን ሳይጨርስ እንዲለቀቅ የተላለፈውን ውሳኔ ይግባኝ ማለቱን አሁን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። የወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ጠበቆች ተቃውሟቸውን ለፍርድ ቤት የሚያስገቡ ቢሆንም ጉዳዩ እስኪታይ ድረስ ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም። የእስር ቤቱ ባለሥልጣናት ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን ለቅጣት የተዘጋጀ ክፍል ውስጥ ለአሥር ቀናት ያህል እንዲቆይ አድርገዋል። ሁኔታዎች ሳይታሰብ መልካቸውን ቢቀይሩም ወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰን አሁንም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ለወንድም ዴኒስ ክሪስተንሰንና ለባለቤቱ ዘወትር ስለምትጸልዩላቸው በጣም እናመሰግናችኋለን።