ጥቅምት 31, 2023
ሩሲያ
“አውሎ ነፋሱን አትይ”
በክራስኖዳር ክልል የሚገኘው የሶቭየትስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ከወንድም አሌክሲ ሌሊኮቭ ክስ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔውን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍበት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
በወንድማማች ማኅበራችን ውስጥ የምናገኛቸው የጽናት ምሳሌዎች ይሖዋ የሚያጋጥመንን የጭንቀት ‘አውሎ ነፋስ እንደሚያስቆም’ በገባው ቃል ላይ ያለንን እምነት ያጠናክሩልናል።—መዝሙር 107:28, 29
የክሱ ሂደት
ጥር 20, 2022
የክስ ፋይል ተከፈተ
ጥር 28, 2022
የእነ ወንድም አሌክሲ ቤት ተፈተሸ። አሌክሲ ለምርመራ ተወስዶ በዚያኑ ቀን ተለቀቀ
የካቲት 16, 2023
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ