በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ሶና ኦሎፖቫ

ጥር 30, 2024
ሩሲያ

እህት ሶና ኦሎፖቫ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሁለት ዓመት የጉልበት ሥራ እንድትሠራ ተፈረደባት

እህት ሶና ኦሎፖቫ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሁለት ዓመት የጉልበት ሥራ እንድትሠራ ተፈረደባት

ጥር 25, 2024 በሰማረ ክልል በቶልያቲ የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ሶና ኦሎፖቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል፤ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሁለት ዓመት የጉልበት ሥራ እንድትሠራ ፈርዶባታል። በማረሚያ ቤቱ ውስጥ እየኖረች ማኅበራዊ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባታል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለሶናም ሆነ በእሱ ለሚታመኑ ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ፍቅራዊ አመራር መስጠቱንና ጥበቃ ማድረጉን እንደሚቀጥል እንተማመናለን።​—መዝሙር 86:2

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 15, 2023

    የወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  2. ግንቦት 16, 2023

    ቤቷ ተፈተሸ። ምርመራ ተካሄደባት እንዲሁም የጉዞ ገደብ ተጣለባት

  3. መስከረም 6, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  4. ጥር 25, 2024

    ጥፋተኛ ናት ተብላ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሁለት ዓመት የጉልበት ሥራ እንድትሠራ ተፈረደባት

a ለእህት ሶና ኦሎፖቫ ቃል መጠይቅ የተደረገላት ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ነው።