በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ቪክቶሪያ ቨርክሆቱሮቫ

ነሐሴ 18, 2021
ሩሲያ

እህት ቪክቶሪያ ቨርክሆቱሮቫ ሊፈረድባት ቢችልም ደስታዋን ጠብቃለች

እህት ቪክቶሪያ ቨርክሆቱሮቫ ሊፈረድባት ቢችልም ደስታዋን ጠብቃለች

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 29, 2021 በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የፕሪኦክስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት ቪክቶሪያ ቨርክሆቱሮቫን ጥፋተኛ ናት በማለት የአራት ዓመት የገደብ እስራት በየነባት። እርግጥ አሁን እስር ቤት አትገባም

  2. ሐምሌ 17, 2020

    በቪክቶሪያ ላይ የጉዞ እገዳ ተጣለባት

  3. መጋቢት 26, 2020

    በቪክቶሪያ ላይ የወንጀል ክስ ተመሠረተባት

  4. ሐምሌ 17, 2019

    አሥር ሕግ አስከባሪ ባለሥልጣናት ከአንድ መርማሪ ጋር በመሆን ቤቷን ለአምስት ሰዓት ፈተሹ። ቪክቶሪያን እና ባለቤቷን ሰርጌን የተለያየ ክፍል ውስጥ አቆዩአቸው። ባለሥልጣናቱ እስር ቤት ውስጥ ያለውን አስከፊ ሁኔታ ለቪክቶሪያ በመንገር ሊያስፈራሯት ሞከሩ

አጭር መግለጫ

በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ስደት ቢደርስባቸውም በይሖዋ እርዳታ ደስታቸውን መጠበቅ ችለዋል። ይሖዋ ለእነዚህ ውድ ወንድሞቻችን “ደስታንና ሰላምን” መስጠቱን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን።—ሮም 15:13