በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት አና ሎክቪትስካያ ፍርድ ቤቱ ፊት ለፊት ቆማ፣ ጥቅምት 2020

የካቲት 25, 2021
ሩሲያ

እህት አና ሎክቪትስካያ ጥፋተኛ ተብላ ሊፈረድባት ይችላል፤ ባለቤቷና አማቷም ክስ ተመሥርቶባቸዋል

እህት አና ሎክቪትስካያ ጥፋተኛ ተብላ ሊፈረድባት ይችላል፤ ባለቤቷና አማቷም ክስ ተመሥርቶባቸዋል

ወቅታዊ መረጃ | የሩሲያ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ

በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው ፍርድ ቤት፣ ታኅሣሥ 16, 2021 የእህት አና ሎክቪትስካያን የይግባኝ ጥያቄ ውድቅ አደረገ። እርግጥ እህት አና አሁን ወህኒ አትወርድም።

ሩሲያ ውስጥ በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣን አውራጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 20, 2021 እህት አና ሎክቪትስካያ ጥፋተኛ ናት በማለት የሁለት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት በይኖባታል።

አጭር መግለጫ

አና ሎክቪትስካያ

  • የትውልድ ዘመን፦ 1993 (ቢሮቢድዣን)

  • ግለ ታሪክ፦ ያሳደገቻት እናቷ ስትሆን በመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች እንድትመራ አሠልጥናታለች። አና በ2012 ተጠመቀች። ጎበዝ ልብስ ሰፊ ናት። በ2018 ከአርተር ጋር ተጋቡ። ባልና ሚስቱ ዓሣ ማጥመድ፣ ወደተለያዩ ቦታዎች መጓዝና መረብ ኳስ መጫወት ያስደስታቸዋል

የክሱ ሂደት

የካቲት 6, 2020 የሩሲያ ባለሥልጣናት፣ በጽንፈኝነት እንቅስቃሴ ተካፍለዋል በማለት ክስ ከመሠረቱባቸው በቢሮቢድዣን ከተማ የሚገኙ ስድስት እህቶች መካከል አና አንዷ ናት። በዚያ አካባቢ የሚገኙ 19 የይሖዋ ምሥክሮች ክስ ተመሥርቶባቸዋል፤ ከእነሱ መካከል የአና ባለቤት አርተርና አማቷ አይሪናም ይገኙበታል።

እነዚህ ክሶች በባልና ሚስቱ ላይ ብዙ ችግር አስከትለዋል። ወደ ሌላ ቦታ መጓዝና የባንክ ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ አይችሉም፤ እንዲሁም በማኅበራዊ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ታግደዋል። በዚህም ምክንያት አና በከፍተኛ ውጥረት የተዋጠች ሲሆን በተደጋጋሚ ሕክምና ማግኘት አስፈልጓታል።

አና ሁኔታውን ለመቋቋም የረዳት ምን እንደሆነ ስትገልጽ እንዲህ ብላለች፦ “በብሮድካስቶቻችን ውስጥ የሚገኙት መዝሙሮች ስሜቴን ያረጋጉልኛል። ምክንያቱም እነዚህ መዝሙሮች ዘና እንድል ብቻ ሳይሆን ስለሚያጋጥሙኝ ሁኔታዎች ትክክለኛውን አመለካከት እንድይዝም ይረዱኛል። አዘውትሬ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረጌም አእምሮዬ በአዎንታዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ረድቶኛል።”

በተጨማሪም አና፣ እሷና አርተር ከራሳቸው ይልቅ የሌሎችን ፍላጎት ለማስቀደም እንደሚጥሩ ተናግራለች። እንዲህ ብላለች፦ “በየወሩ ትንሽ ነገርም ቢሆን ለሰዎች ስጦታ ለመስጠት ግብ አውጥተናል። ስለ ራሳችን ችግር ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ሰዎችም ለማሰብ እንሞክራለን።”

አና የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እየተጠባበቀች ሲሆን ይህን ሁኔታ ‘ለይሖዋ ታማኝ መሆኗን’ በተግባር ለማሳየት የሚያስችል ግሩም አጋጣሚ እንደሆነ አድርጋ ትመለከተዋለች።—መዝሙር 18:25