መጋቢት 6, 2024
ሩሲያ
እህት የሌና ኮዤቭኒኮቫ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባት
መጋቢት 4, 2024 በሰማረ ክልል በቶልያቲ የሴንትራልኒ አውራጃ ፍርድ ቤት እህት የሌና ኮዤቭኒኮቫ ጥፋተኛ ናት የሚል ብይን አስተላልፏል። የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አትወርድም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ለየሌናም ሆነ ስደት እየደረሰባቸው ላሉት ሌሎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘በመንፈሱ አማካኝነት ኃይል’ በመስጠት ጸሎታችንን ስለሚመልስልን አመስጋኞች ነን።—ኤፌሶን 3:16
የክሱ ሂደት
ግንቦት 15, 2023
የወንጀል ክስ ተመሠረተ
ግንቦት 16, 2023
ቤቷ ተፈተሸ
ግንቦት 18, 2023
የጉዞ ገደብ ተጣለባት
ነሐሴ 16, 2023
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
መጋቢት 4, 2024
ጥፋተኛ ነች ተብላ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተፈረደባት
a እህት ኮዤቭኒኮቫ ሐሳብ የሰጠችው ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ነው።