በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት የሌና ሳቨልዬቫ

ጥቅምት 28, 2021
ሩሲያ

ከአስተማሪነት ጡረታ የወጡ የ80 ዓመት አረጋዊት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በመናገራቸው ስደት ደረሰባቸው

ከአስተማሪነት ጡረታ የወጡ የ80 ዓመት አረጋዊት ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በመናገራቸው ስደት ደረሰባቸው

ወቅታዊ መረጃ | የሩሲያ ፍርድ ቤት እህት የሌና ሳቨልዬቫ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

የካቲት 14, 2022 የቶምስክ ክልላዊ ፍርድ ቤት እህት የሌና ሳቨልዬቫ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። እርግጥ እህት የሌና አሁን እስር ቤት አይገቡም።

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 17, 2021

    በቶምስክ ክልል የሚገኘው የሰይቨርስኪ ከተማ ፍርድ ቤት እህት የሌና ሳቨልዬቫን ጥፋተኛ ናቸው በማለት የአራት ዓመት የገደብ እስራት በይኖባቸዋል። ቀደም ሲል አቃቤ ሕጉ የ500,000 ሩብል (7,198 የአሜሪካ ዶላር) መቀጮ እንዲከፍሉ መጠየቁ ይታወሳል።

  2. ሐምሌ 22, 2021

    ፍርድ ቤቱ ክሱን መስማት ጀመረ

  3. መጋቢት 25, 2021

    የሩሲያ አቃቤ ሕጎች በእህት የሌና ላይ የወንጀል ክስ መሠረቱ። እህት የሌና በሩሲያ ፌዴሬሽን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 282.2 መሠረት ሰዎች “በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማሳመን፣ በመመልመል ወይም በማነሳሳት” ወንጀል ተከሰዋል።

    ለክሱ መነሻ የሆነው ከእህት የሌና ጋር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት ያደረጉ ሁለት ሴቶች የሰጡት ምሥክርነት ነው፤ አንደኛዋ የፌዴራል ደህንነት ቢሮ አባል ስትሆን ሌላኛዋ ደግሞ የሩሲያ ብሔራዊ ዘብ አባል ነች። እነዚህ ሴቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የመወያየት ፍላጎት ያላቸው አስመስለው ከእህት የሌና ጋር ያደረጉትን ውይይት በሚስጥር ቀድተው ነበር፤ ከዚያም ስለ እሳቸውና ስለ እምነት አጋሮቻቸው መረጃ ለመንግሥት ባለሥልጣናት አቀብለዋል።

አጭር መግለጫ

እህት የሌና ስደት ሲደርስባቸው ያሳዩት ቆራጥነት ያበረታታናል። ‘በምሥራቹ ላይ ያላቸውን እምነት ጠብቀው ለመኖር በአንድ መንፈስ ጸንተው የሚቆሙትንና በምንም መንገድ በጠላቶቻቸው የማይሸበሩትን’ በሙሉ ይሖዋ እንደማይረሳቸው እርግጠኞች ነን።—ፊልጵስዩስ 1:27, 28