ሐምሌ 22, 2022 | የታደሰው፦ ጥር 30, 2024
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | በሹያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች የደረሰባቸውን ግፍ ተቋቁመዋል
ጥር 29, 2024 በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የሹያ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም አሌክሲ አርሂፖቭ፣ ወንድም ዲሚትሪ ሚኻይሎቭ እና ባለቤቱ የሌና እንዲሁም እህት ስቬትላና ርዥኮቭ እና እህት ስቬትላና ሺሺና ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። አሌክሲ የ350,000 ሩብል (3,920 የአሜሪካ ዶላር)፣ ዲሚትሪ የ950,000 ሩብል (10,640 ዶላር)፣ የሌና የ560,000 ሩብልስ (6,270 ዶላር) ስቬትላና ርዥኮቭ የ480,000 ሩብል (5,380 ዶላር) እና ስቬትላና ሺሺና የ400,000 ሩብል (4,480 ዶላር) መቀጮ ተፈርዶባቸዋል።
የክሱ ሂደት
መስከረም 21, 2017
ዳኛው የወንድም ዲሚትሪ ሚኻይሎቭ እና የባለቤቱ ስልክ እንዲጠለፍ ፈቃድ ሰጠ
ጥር 15, 2018
ዳኛው የእህት ስቬትላና ርዥኮቭ ስልክ እንዲጠለፍ እንዲሁም ቤቷ በቪዲዮ ካሜራ እየታየ ክትትል እንዲደረግበት ፈቃድ ሰጠ
ሚያዝያ 20, 2018
ባለሥልጣናቱ የአምስቱንም የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ፈተሹ
ግንቦት 29, 2018
ፖሊሶች ዲሚትሪን ከያዙት በኋላ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል ከሰሱት። ከዚያም ማረፊያ ቤት እንዲቆይ ተደረገ
ሰኔ 22, 2018
አሌክሲም በክሱ ውስጥ እንዲካተት ተደረገ፤ አካባቢውን ለቅቆ እንዳይሄድ ታገደ
ሰኔ 27, 2018
እህት የሌና ሚኻይሎቭ፣ እህት ስቬትላና ርዥኮቭ እና እህት ስቬትላና ሺሺና በክሱ ውስጥ ተካተቱ
ኅዳር 15, 2018
ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ዲሚትሪ ከማረፊያ ቤት እንዲለቀቅ ወሰነ፤ በዚያ ለስድስት ወራት ገደማ ቆይቷል
ነሐሴ 10, 2021
ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ
መስከረም 16, 2021
ጉዳዩን አቃቤ ሕጉ እንዲመለከተው ወደ እሱ ተመለሰ
ግንቦት 25, 2022
የክሱ ሂደት ቀጠለ
አጭር መግለጫ
በሩሲያ ያሉ ውድ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የሚያሳዩት ድፍረትና ጽናት የደስታ ምንጭ ሆኖልናል።—1 ተሰሎንቄ 2:20