በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ቫሲችኪን፣ ወንድም ሰርጌ ጋልያሚን፣ ወንድም አናቶሊ ልያሞ እና ወንድም ቭላዲሚር ስፒቫክ

ግንቦት 30, 2023 | የታደሰው፦ መጋቢት 6, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | በቴይኮቮ የሚገኙ ወንድሞች ትኩረት ያደረጉት በይሖዋ እርዳታ ላይ ነው

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | በቴይኮቮ የሚገኙ ወንድሞች ትኩረት ያደረጉት በይሖዋ እርዳታ ላይ ነው

የካቲት 29, 2024በኢቫኖቮ ክልል የሚገኘው የቴይኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ሰርጌ ጋልያሚን፣ ወንድም አናቶሊ ልያሞ፣ ወንድም ቭላዲሚር ስፒቫክ እና ወንድም አሌክሳንደር ቫሲችኪን ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሁሉም ወንድሞች የገንዘብ መቀጮ ተጥሎባቸዋል። ቭላዲሚር 600,000 ሩብል (6,564 የአሜሪካ ዶላር)፣ ሰርጌ 650,000 ሩብል (7,111 የአሜሪካ ዶላር) እንዲሁም አሌክሳንደር እና አናቶሊ 1,100,000 ሩብል (12,034 የአሜሪካ ዶላር) እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ ካዘጋጀው በረከት ጋር ሲነጻጸር በዚህ ሥርዓት የሚደርስብን ማንኛውም ፈተና ጊዜያዊ እንደሆነ እናውቃለን።—2 ቆሮንቶስ 4:17, 18

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 10, 2020

    የክስ ፋይል ተከፈተ

  2. ሚያዝያ 11, 2020

    ቤታቸው ተፈተሸ

  3. ሚያዝያ 16, 2020

    የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው

  4. የካቲት 2, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ