በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ኦሌግ ኮንሺን፣ ወንድም ሰርጌ ማልያኖቭ እና እህት ስቬትላና ማልያኖቫ

ኅዳር 28, 2022 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 27, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | በይሖዋ በመታመን ጭንቀትን ማሸነፍ

ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | በይሖዋ በመታመን ጭንቀትን ማሸነፍ

ሚያዝያ 26, 2023 በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኦሌግ ኮንሺን፣ ወንድም ሰርጌ ማልያኖቭ እና ወንድም ሮማን ዢቮሉፖቭ a እንዲሁም እህት ስቬትላና ማልያኖቫ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል፤ ስቬትላና ማልያኖቫ የወንድም ሰርጌ ማልያኖቭ ልጅ ነች። ፍርድ ቤቱ ከ450,000 ሩብል (5,494 የአሜሪካ ዶላር) እስከ 700,000 ሩብል (8,546 የአሜሪካ ዶላር) የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንዲከፍሉ በይኗል።

አጭር መግለጫ

‘ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ’ ሁሉ ‘ደፋርና ልበ ጽኑ’ ናቸው፤ ስደትን በታማኝነት እየተጋፈጡ ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ለዚህ ሕያው ማስረጃዎች ናቸው።—መዝሙር 27:14

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 7, 2019

    አንድ ዳኛ፣ በሰርጌ የስልክ ጥሪዎችና ሌሎች የኤሌክትሮኒክ መገናኛ መንገዶች ላይ የክትትል ትእዛዝ አወጡ

  2. ሐምሌ 16-17, 2019

    ፖሊሶች በኒዥኒ ኖቭጎሮድ እና በክልሉ የሚኖሩ 31 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ። ኦሌግ፣ ሰርጌ እና ስቬትላና በቁጥጥር ሥር ውለው ወደ ጣቢያ ተወሰዱ። ከዚያም የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  3. ሐምሌ 18, 2019

    ኦሌግ፣ ሰርጌ እና ስቬትላና ከጣቢያ ተለቀቁ። ሁለቱ ወንድሞች በተወሰኑ ሰዓታት ላይ ከቤት እንዳይወጡ፣ በማንኛውም የመገናኛ ዘዴ ከሌሎች ጋር እንዳያወሩና ኢንተርኔት እንዳይጠቀሙ የፍርድ ቤት እግድ ወጣባቸው

  4. ነሐሴ 24, 2021

    ሮማን በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ ተካፍለሃል ተብሎ ተከሰሰ፤ የጉዞ ክልከላዎችም ተጣሉበት

  5. መጋቢት 3, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

a b ይህ ርዕስ በተዘጋጀበት ወቅት የወንድም ሮማን ዢቮሉፖቭን ፎቶግራፍ ማግኘት አልተቻለም።