የካቲት 21, 2022 | የታደሰው፦ ሐምሌ 31, 2023
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ—መቀጮ ተጣለባቸው | ከእምነት አጋሮቻቸው ያገኙት ድጋፍ እምነታቸውን አጠናክሮላቸዋል
ሐምሌ 28, 2023 በካሬሊያ ሪፑብሊክ የሚገኘው የፔትሮዛቮድስክ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ማክሲም አሞሶቭ፣ ወንድም ሚካኼል ጎርድዬቭ፣ ወንድም ኒኮላይ ሌሼንኮ እና ወንድም ዲሚትሪ ራቭኑሽኪን ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ወንድሞች ከ450,000 ሩብል (4,909 የአሜሪካ ዶላር) እስከ 500,000 ሩብል (5,455 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ ተጥሎባቸዋል።
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 31, 2019
የፌዴራል ደህንነት አባላት የ16 የይሖዋ ምሥክሮችን ቤቶችና የሥራ ቦታዎች ፈተሹ
ነሐሴ 2, 2019
መርማሪው፣ ማክሲም አገር ለቆ እንዳይወጣ አገደ። ባለሥልጣናቱ በኒኮላይ ላይ የወንጀል ምርመራ የጀመሩ ሲሆን አካባቢውን ለቆ እንዳይሄድ እገዳ ጣሉበት
ነሐሴ 6, 2019
መርማሪው፣ በማክሲም እና በኒኮላይ ላይ ክስ መሠረተ፤ ወንጀላቸው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናታቸው ነው
መስከረም 5, 2019
የፌዴራል ደህንነት አባላት ሚካኼልን ሥራ ቦታው ሄደው በቁጥጥር ሥር አዋሉት፤ ኮምፒውተሩንም ወሰዱበት። መርማሪው በሚካኼል ላይ የወንጀል ምርመራ ጀመረ
መስከረም 20, 2019
የፌዴራል ደህንነት አባላት የዲሚትሪን የሥራ ቦታ ፈተሹ፤ ስልኩንም ወሰዱበት። መርማሪው ዲሚትሪን ለአራት ሰዓት ያህል መረመረው፤ በእሱ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲከፈት ያደረገ ሲሆን አካባቢውን ለቆ እንዳይሄድ አዘዘው
ጥቅምት 18, 2021
ክሱ መታየት ጀመረ
አጭር መግለጫ
በሩሲያ ያሉ ወንድሞቻችን ስደት ቢደርስባቸውም በእውነት ውስጥ እየተመላለሱ በመሆናቸው እንኮራባቸዋለን።—3 ዮሐንስ 4