በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በኒዥኒ ኖቭጎሮድ የሚገኘው የሞስኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ሕንፃ፤ በስተ ቀኝ፦ ወንድም ማክሲም ዛቭራዥኖቭ

ሚያዝያ 20, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | ማክሲም ዛቭራዥኖቭ አዎንታዊ አመለካከት ይዞ ቀጥሏል

ወቅታዊ መረጃ | ማክሲም ዛቭራዥኖቭ አዎንታዊ አመለካከት ይዞ ቀጥሏል

ግንቦት 30, 2022 በኒዥኒ ኖቭጎሮድ ከተማ የሚገኘው የሞስኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ማክሲም ዛቭራዥኖቭ ጥፋተኛ ነው በማለት የስድስት ዓመት የገደብ እስራት በየነበት። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. ሰኔ 4, 2019

    የወንጀል ምርመራ ተጀመረ

  2. ሐምሌ 17, 2019

    የጽንፈኝነት እንቅስቃሴዎችን በማደራጀት ወንጀል ተከሰሰ። በቁጥጥር ሥር ውሎ የወንጀል ምርመራ ተደረገበት፤ እንዲሁም ሌሊቱን ማረፊያ ቤት ቆየ

  3. ሐምሌ 18, 2019

    አንዳንድ እገዳዎች ተጣሉበት፤ ስልክም ሆነ ኢንተርኔት መጠቀም እንዲሁም ከምሽቱ 3:00 እስከ ጠዋቱ 3:00 ድረስ ከቤቱ መውጣት ተከለከለ

  4. የካቲት 3, 2020

    የተጣለበት እገዳ ተነሳለት

  5. የካቲት 26, 2020

    አካባቢውን ለቅቆ እንዳይሄድ የጉዞ እገዳ ተጣለበት

  6. ታኅሣሥ 6, 2021

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

በሩሲያና በክራይሚያ የሚኖሩ ውድ ወንድሞቻችን የሚደርስባቸው ስደት ቢቀጥልም በይሖዋ ላይ ያለን እምነት ተጠናክሯል። እሱ ታማኞቹን መቼም ቢሆን እንደማይተዋቸው እርግጠኞች ነን።—ዕብራውያን 13:5