በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ፓቬል ፖፖቭ

ግንቦት 25, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ | “ምን የሚያስፈራኝ ነገር አለ?”

ወቅታዊ መረጃ | “ምን የሚያስፈራኝ ነገር አለ?”

ግንቦት 25, 2022 በቼልያቢንስክ የሚገኘው የሜተለርጂቼስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ወንድም ፓቬል ፖፖቭ ጥፋተኛ ነው ብሎ የስድስት ዓመት የገደብ እስር ፈርዶበታል። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።

የክሱ ሂደት

  1. መጋቢት 26, 2019

    ጭንብል ያጠለቁ እንዲሁም አውቶማቲክ ጠመንጃና ትልቅ መዶሻ የያዙ አሥር ሰዎች የፓቬልን ቤት ሰብረው ገብተው በረበሩ

  2. ሚያዝያ 22, 2021

    የወንጀል ክስ ተመሠረተበት

  3. ግንቦት 18, 2021

    ፖሊሶች ለሁለተኛ ጊዜ የፓቬልን ቤት ፈተሹ። የፓቬል ባለቤት የሌና እና የ13 ዓመት ሴት ልጃቸው ለምርመራ ተወሰዱ

  4. ነሐሴ 31, 2021

    የሽብርተኞችና የጽንፈኞች ስም ዝርዝር በሚገኝበት መዝገብ ላይ ተካተተ

  5. ኅዳር 29, 2021

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ወንድሞቻችን ከአቋማቸው ፍንክች ሳይሉ ፈተናን በድፍረት መጋፈጣቸውን ቀጥለዋል፤ ይሖዋም እነዚህን ታማኝ አገልጋዮቹን እንደሚደግፋቸውና ወሮታቸውን እንደሚከፍላቸው እርግጠኞች ነን።—2 ሳሙኤል 22:19-21