በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ናዴዥዳ ኮሮቦችኮ፣ ወንድም ኢጎር ክሌትኪን እና ወንድም ኒኮላይ ኮኖኔንኮ

ሚያዝያ 1, 2024 | የታደሰው፦ ሐምሌ 30, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ተፈረደባቸው | “እጅ መስጠት አማራጭ አይደለም”

ወቅታዊ መረጃ—ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ተፈረደባቸው | “እጅ መስጠት አማራጭ አይደለም”

ሐምሌ 30, 2024 በካባሮቭስክ ግዛት የሚገኘው የኒኮላዬቭስክ ኦን አሙር ከተማ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ኢጎር ክሌትኪን፣ ወንድም ኒኮላይ ኮኖኔንኮ እና እህት ናዴዥዳ ኮሮቦችኮ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ኢጎር እና ኒኮላይ የስድስት ዓመት ናዴዥዳ ደግሞ የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል።አሁን ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ የሚታመኑበትን እና “አንተ አምላኬ ነህ” የሚሉትን ሁሉ በፍቅር ስለሚንከባከብና ስለሚደግፋቸው እናመሰግነዋለን።​—መዝሙር 31:14

የክሱ ሂደት

  1. ጥቅምት 11, 2021

    የኢጎር እና የናዴዥዳ ቤቶች ተፈተሹ። ኢጎር ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ

  2. ጥቅምት 12, 2021

    ናዴዥዳ ምርመራ ተደረገባት

  3. ጥቅምት 13, 2021

    ኢጎር ከጣቢያ ተለቀቀ

  4. ጥቅምት 14, 2021

    ኢጎር እና ናዴዥዳ የጉዞ ገደቦች ተጣሉባቸው

  5. መስከረም 27, 2022

    ኒኮላይ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  6. ጥር 16, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ