በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዴኒስ ሜርኩሎቭ እና ባለቤቱ ናታሊያ

ታኅሣሥ 27, 2022 | የታደሰው፦ መጋቢት 27, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ቅጣት ተጣለበት | “ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ይሖዋ ጠንካራ ያደርገናል”

ወቅታዊ መረጃ—ቅጣት ተጣለበት | “ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ይሖዋ ጠንካራ ያደርገናል”

መጋቢት 23, 2023 በሙርማንስክ ክልል የሚገኘው የአፓቲቲ ከተማ ፍርድ ቤት ወንድም ዴኒስ ሜርኩሎቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ብይን አስተላልፏል። የ500,000 ሩብልስ ($6,485.00 የአሜሪካ ዶላር) ቅጣት ተጥሎበታል።

አጭር መግለጫ

ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን የሚያጽናናን አንድ ነገር አለ፤ ይሖዋን የቅርብ ወዳጃችን ካደረግነውና ከታመንንበት ‘ያጠነክረናል፤ አጽንቶም ያቆመናል።’—1 ጴጥሮስ 5:10

የክሱ ሂደት

  1. ሐምሌ 21, 2021

    በአፓቲቲ እና በአቅራቢያዋ ያሉ 14 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ተፈተሹ። የፌዴራል የደህንነት ፖሊሶች የእነዴኒስን መኖሪያ ቤት በኃይል ሰብረው ከገቡ በኋላ ባልና ሚስቱን ለጥያቄ ወሰዷቸው። ከሌሊቱ 10:00 ላይ ለቀቋቸው

  2. ሐምሌ 22, 2021

    ፖሊሶቹ፣ ዴኒስ ወደ መርማሪው ቢሮ ተመልሶ እንዲመጣ ጠሩት። ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ

  3. ሐምሌ 23, 2021

    ከጣቢያ ተለቅቆ የቁም እስረኛ ተደረገ

  4. መስከረም 17, 2021

    ከቁም እስር ተፈታ፤ የጉዞ ክልከላዎች ተጣሉበት

  5. ሐምሌ 15, 2022

    “መዝሙር ዘምረሃል” እንዲሁም “ወደ ይሖዋ አምላክ ጸልየሃል” በሚል በይፋ ክስ ተመሠረተበት፤ የተወነጀለበት ክስ የጽንፈኛ ድርጅትን እንቅስቃሴ ማስተባበር የሚል ነው

  6. መስከረም 20, 2022

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ