ኅዳር 2, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | በሳካሊን ስደት የደረሰባቸው አምስት ክርስቲያኖች በይሖዋ ድጋፍ ታምነዋል
ግንቦት 11, 2022 የሳካሊን ክልላዊ ፍርድ ቤት ወንድም ቭያቼስላቭ ኢቫኖቭ፣ ወንድም አሌክሳንደር ኮዝሊቲን፣ ወንድም ሰርጌ ኩላኮቭ፣ እህት ታትያና ኩላኮቫ እና ወንድም ዬቭጌኒ ዬሊን ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አደረገ። እርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።
ጥር 31, 2022 በሳካሊን ክልል የሚገኘው የኔቬልስኪ ከተማ ፍርድ ቤት ቭያቼስላቭ፣ አሌክሳንደር፣ ሰርጌ፣ ታትያና እና ዬቭጌኒ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላለፈ። ሰርጌ እና ዬቭጌኒ የስድስት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። ቭያቼስላቭ፣ አሌክሳንደር እና ታትያና ደግሞ የሁለት ዓመት የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል።
የክሱ ሂደት
ሐምሌ 2020
ቭያቼስላቭ፣ አሌክሳንደር፣ ሰርጌ እና ታትያና የጉዞ እገዳ ተጣለባቸው
ሚያዝያ 2, 2020
ዬቭጌኒ የጉዞ እገዳ ተጣለበት
ጥር 20, 2019
የፌዴራል ደህንነት (የሩሲያ የሚስጥር ፖሊስ) አባላት የይሖዋ ምሥክር ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ቢያንስ የ11 ዜጎችን ቤት በረበሩ። ፖሊሶቹ በቁጣ ተሞልተው የነበረ ሲሆን ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችንም ጭምር የወንጀል ምርመራ አካሂደውባቸዋል። ይህ የሆነው የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በይሖዋ ምሥክሮች ላይ እየደረሰ ያለውን ስደት ለማጣራት ቃል ከገቡ ብዙም ሳይቆይ ነው
አጭር መግለጫ
ይሖዋ ውድ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መንከባከቡን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን፤ እነሱም እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ “አምላክ አዳኜ ነው! በእሱ እታመናለሁ፤ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም” ይላሉ።—ኢሳይያስ 12:2