ታኅሣሥ 20, 2021
ሩሲያ
ወቅታዊ መረጃ | በትራንስ ባይካል ክልል ከዚህ በፊት ተደርጎ የማያውቅ የቤት ብርበራ ከተደረገ በኋላ አራት ወንድሞች የፍርድ ውሳኔያቸውን እየተጠባበቁ ነው
መስከረም 20, 2022 የትራንስ ባይካል ክልል ፍርድ ቤት ወንድም ቭላዲሚር ዬርሞላዬቭ፣ ወንድም ሰርጌ ኪሪልዩክ፣ ወንድም ኢጎር ማማሊሞቭና ወንድም አሌክሳንደር ፑቲንትስዬቭ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል። ቭላዲሚር፣ ኢጎርና አሌክሳንደር እስር ቤት ይቆያሉ። ሰርጌ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም።
ሰኔ 6, 2022 የቺታ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ቭላዲሚር፣ ሰርጌ፣ ኢጎርና አሌክሳንደር ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ሰርጌ የስድስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶበታል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርድም። ቭላዲሚር፣ ኢጎርና አሌክሳንደር እያንዳንዳቸው የስድስት ዓመት ተኩል እስራት ተፈይኖባቸዋል። ወዲያውኑ ወህኒ ወርደዋል።
የክሱ ሂደት
መጋቢት 16, 2021
የክስ ሂደቱ ጀመረ
የካቲት 2, 2021
ቭላዲሚር፣ ሰርጌ፣ ኢጎርና አሌክሳንደር የታገደን ድርጅት እንቅስቃሴ በማደራጀት ወንጀል ተከሰሱ
ሚያዝያ 3, 2020
ቭላዲሚር ከቁም እስር ተለቀቀ
የካቲት 15, 2020
ሰርጌ ለአምስት ቀናት ከታሰረ በኋላ ነፃ ተለቀቀ
የካቲት 12, 2020
ኢጎር እና አሌክሳንደር ከእስር ተለቀቁ። ሰርጌ ለተጨማሪ 72 ሰዓታት ታሰረ። ቭላዲሚር ለ52 ቀናት በቁም እስር እንዲቆይ ተፈረደበት
የካቲት 10, 2020
የፌደራል ደህንነት አገልግሎት አባላት በትራንስ ባይካል ክልል በሚገኙ 50 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ላይ ፍተሻ አካሄዱ። ከተፈተሹት ቤቶች መካከል በዕድሜ የገፉና የአካል ጉዳት ያለባቸው የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ይገኛሉ። በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የይሖዋ ምሥክር የሆነ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ በእናቱና በታናሽ እህቱ ፊት ተደብድቧል። አንድ ወንድም ከባድ አካላዊ ሥቃይ ደርሶበታል። የደህንነት አባላቱ ብርበራውን ከጨረሱ በኋላ ኢጎርን፣ አሌክሳንደርን፣ ሰርጌንና ቭላዲሚርን ጨምሮ አሥር ወንድሞችን አሰሩ
አጭር መግለጫ
ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ባለሥልጣናት ከፍተኛ ጫና ቢያሳድሩባቸውም ጠንካራ እምነት አሳይተዋል። ልክ እንደ ዳንኤልና ሦስቱ ጓደኞቹ ለይሖዋ ታማኝ ሆነው ለመቀጠል ‘በልባቸው ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል’፤ እኛም የእነሱን ምሳሌ እንከተል።—ዳንኤል 1:8