በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ዲሚትሪ ሴሞኖቭ እና ባለቤቱ ናዴዥዳ

ኅዳር 4, 2022
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ባልና ሚስቱ ተፈረደባቸው | ከመጽሐፍ ቅዱስ የእምነት ምሳሌዎች ብርታት ማግኘት

ወቅታዊ መረጃ—ባልና ሚስቱ ተፈረደባቸው | ከመጽሐፍ ቅዱስ የእምነት ምሳሌዎች ብርታት ማግኘት

ኅዳር 8, 2022 በካምቻትካ ክልል የሚገኘው የፔትሮፓቭሎቭስክ-ካምቻትስኪ ከተማ ፍርድ ቤት በወንድም ዲሚትሪ ሴሞኖቭ እና በባለቤቱ በናዴዥዳ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። በሁለቱም ላይ የአራት ዓመት የገደብ እስራት በይኗል። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. መስከረም 3, 2021

    ከዲሚትሪና ከናዴዥዳ ጋር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውይይት የምታደርግ አንዲት ሴት ለፌዴራል ደህንነት አባላት መረጃ ማቀበል ጀመረች። እሷ ባቀበለችው መረጃ ላይ የተመረኮዘ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው። ሌሎች ሰዎች ጽንፈኛ ድርጅትን እንዲቀላቀሉና በእንቅስቃሴዎቹ እንዲሳተፉ ቀስቅሰዋል በሚል ተከሰሱ

  2. መስከረም 6, 2021

    መኖሪያ ቤታቸው ተፈተሸ። ለምርመራ ተወሰዱ፤ የጉዞ እገዳም ተጣለባቸው

  3. ሐምሌ 26, 2022

    ጉዳያቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ዲሚትሪ እና ናዴዥዳ በራሳቸው ሕይወት እንዳዩት ይሖዋ ስደት የሚደርስባቸው አገልጋዮቹን ደፋርና ጠንካራ እንዲሆኑ ይረዳቸዋል። መቼም ቢሆን አይተዋቸውም።—ኢያሱ 1:9