በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ኦሌግ ፖስትኒኮቭ እና ባለቤቱ አግኔሳ

ታኅሣሥ 23, 2021 | የታደሰው፦ ነሐሴ 29, 2023
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ባልና ሚስቱ ተፈረደባቸው | የይሖዋ ዝግጅቶች ወንድም ኦሌግ እና ባለቤቱ እህት አግኔሳ ውስጣዊ ሰላም እንዲያገኙ ረድተዋቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—ባልና ሚስቱ ተፈረደባቸው | የይሖዋ ዝግጅቶች ወንድም ኦሌግ እና ባለቤቱ እህት አግኔሳ ውስጣዊ ሰላም እንዲያገኙ ረድተዋቸዋል

ነሐሴ 23, 2023 በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ኦሌግ ፖስትኒኮቭ እና በእህት አግኔሳ ፖስትኒኮቫ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ኦሌግ የአምስት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት፣ አግኔሳ ደግሞ የአራት ዓመት ተኩል የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይወርዱም።

ጥቅምት 11, 2022 የአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል ፍርድ ቤት የወንድም ኦሌግ ፖስትኒኮቭን እና የእህት አግኔሳ ፖስትኒኮቫን የጥፋተኝነት ውሳኔ ሽሮታል። ጉዳያቸው ዳግመኛ እንዲታይ ይላካል።

ሚያዝያ 25, 2022 በአይሁዳውያን ራስ ገዝ ክልል የሚገኘው የቢሮቢድዣንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት ኦሌግ እና አግኔሳ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ኦሌግ የአምስት ዓመት ተኩል አግኔሳ ደግሞ የአምስት ዓመት የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። እርግጥ አሁን ወህኒ አይወርዱም።

የክሱ ሂደት

  1. የካቲት 12, 2021

    የፌደራል ደህንነት ቢሮው በእህት አግኔሳ ላይ የወንጀል ክስ መሠረተባት። እህት አግኔሳና ባለቤቷ “የወንጀለኛ” ቡድን በመመሥረትና ስለ ቡድኑ “ጽንፈኛ” ዓላማዎች በማስፋፋት ወንጀል ተከሰሱ። ኦሌግና አግኔሳ ከአካባቢው ርቀው እንዳይሄዱ ታዘዙ፤ የባንክ ሒሳባቸውን እንዳያንቀሳቅሱ ታገዱ፤ እንዲሁም ስማቸው በሩሲያ የአሸባሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

  2. የካቲት 12, 2020

    የፌደራል ደህንነት ቢሮው በኦሌግ ላይ የወንጀል ክስ መሠረተ

አጭር መግለጫ

እነዚህ ተሞክሮዎች ይሖዋ ሕዝቦቹ ስደትን በተሳካ ሁኔታ እንዲወጡ አስቀድሞ እንዳዘጋጃቸው የሚያሳዩ ተጨማሪ ማስረጃዎች ናቸው። እንግዲያው ሁላችንም በይሖዋ ‘ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት’ መታመናችንን እንቀጥል።—መዝሙር 115:1